መቆሚያ ያጣው የመርከዙ የቁልቁለት ጉዞ!
~
የሸሪዐ ቀዳሚ ግብ ጉዳትን ማስወገድ፣ ካልሆነ መቀነስ እንዲሁም ጥቅምን ማስገኘት ነው። አንዳንዴ የከፋውን ሸር ለማለፍ ወይም ለመቀነስ ሲባል ያነሰውን ሸር እንፈፅም ዘንድ ጫና ሊገጥመን ይችላል። በዚህ የተነሳ ለአጠቃላዩ የደዕዋ መስለሐ ሲባል ውስጣችን የማያምንበት ጉዳይ ላይ ልንነካካ እንችላለን። ይሄ ብስለት አልፎም ድፍረት የሚፈልግ ጉዳይ ነው።
በሌላ በኩል ደግሞ ከእለት ወደ እለት መንሸራተቱን በ "መስለሐ" ወረቀት እየጠቀለለ የሚያቀርብ ብኩን አለ። ማዶ ላይ ያለን "መስለሐ" ሲያስብ ዙሪያውን ስላለው ተጨባጭ አያስብም። "የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች" እንደሚባለው ማለት ነው።
የመርከዝ ኢብኑ መስዑድ አካሄድ እዚህ ላይ ነው ያለው። መሪዎቻቸው በዑጅበ ነፍስ የተወጠሩ፣ ቀድራቸውን የማያውቁ፣ "ከኛ ወዲያ መስለሐ እና መፍሰዳ የሚለይ ላሳር" ውስጥ የገቡ ናቸው። ይሄ አዲስ የመጣ ሳይሆን ነባር አመላቸው ነው። በዙሪያቸው ያለው "አገር ለመምራት እድሉ ቢስሰጣቸው መምራት የሚያስችል ብቃት አላቸው" የሚል፣ ቢያጥፉት የሚታጠፍ፣ ቢዘረጉት የሚዘረጋ እንዳሻቸው የሚሰሩት ስብስብ ለራሳቸው የተሳሳተ ግምት እንዲይዙ አድርጓቸዋል። የፈለገ ቢወርዱ "ኧረ አሁንስ በዛ!" የሚል ድፍረት ያለው ከኖረ ከስንት አንድ ነው። እሱውም ከተገኘ። ሰው በዚህ መጠን እንዴት በጋራ ጭፍን ተከታይ ይሆናል? የሚገርም ነው!
ወላሂ! መርከዙን የምታድኑት ኢኽላስን መሰረት ባደረገ እውነተኛ አካሄድ እንጂ በጭፍን ውግንና አይደለም። ሰዎቹንም ሲያጠፉ እጃቸውን በመያዝ እንጂ በጭፍን ብትከላከሉ እነሱንም ላትጠቅሙ ራሳችሁንም ትጎዳላችሁ። ይልቁንም ከዚህ "እናንተን የማይታያችሁ ይታየናል" ከሚል አጉል ግብዝነት እንዲወጡ ብታግዟቸው ነው የሚሻለው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor