Репост из: ሞአ አንበሳ።
ተስፋሽን ፈራሁት!
የደጅሽ አበባ፣ እምቡጥ ሲይዝልሽ፤
የአንቀልባሽ ህጻን፣ ጠብቶ ሲያገሳልሽ፤
ደስታሽን አይቼ፤
ተስፋሽን ቃኝቼ፤
.....ነገሽን ፈራሁት።
እምቡጥ የሚያመክን፣ አመዳይ ትላትል፣ ተምች በሞላበት፤
እምቡጥ የሚቀጥፍ፣ ሰው በሚኖርበት፤
.........በእኔና አንቺ አለም፤
ማንቦጥ መታጨት ነው፣
መውለድ መከተብ ነው፣
.........የዘላለም ሀዘን፣ የዘላለም ህመም።
.....
✍🏽 ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ
©የተስፋ ክትባት
የደጅሽ አበባ፣ እምቡጥ ሲይዝልሽ፤
የአንቀልባሽ ህጻን፣ ጠብቶ ሲያገሳልሽ፤
ደስታሽን አይቼ፤
ተስፋሽን ቃኝቼ፤
.....ነገሽን ፈራሁት።
እምቡጥ የሚያመክን፣ አመዳይ ትላትል፣ ተምች በሞላበት፤
እምቡጥ የሚቀጥፍ፣ ሰው በሚኖርበት፤
.........በእኔና አንቺ አለም፤
ማንቦጥ መታጨት ነው፣
መውለድ መከተብ ነው፣
.........የዘላለም ሀዘን፣ የዘላለም ህመም።
.....
✍🏽 ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ
©የተስፋ ክትባት