"አክሱም ላይ የተከለከለው ሂጃብ ብቻ አይደለም እስልምናም ጭምር ነው"
▣ በፌደራል መጅሊስ የትግራይ ክልል ተወካይ እንዲሁም የትምህርትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ተጠሪ ኢንጅነር አንዋር ሙስጠፋ ለሀሩን ሚድያ ከገለፁት
- ሀሩን ሚድያ፣ ታህሳስ 27/2017
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የትምህርትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ተጠሪ ኢንጅነር አንዋር ሙስጠፋ እንዳሉት ሂጃብ እና እስልምና የማይነጣጠሉ መሆናቸውን አንስተው በአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች ላይ ይህን ያደረጉት አካላት የእስልምና ጥላቻ ያለባቸው መሆኑን ለሀሩን ሚድያ ተናግረዋል።
በአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች በሂጃብ ምክንያት ከትምህርት ገበታ መገለላቸውን አስመልክቶ ፌደራል መጅሊሱ ምን እየሰራ ነው ብለን ለጠየቅናቸው ጥያቄም ከትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጋር በጋራ በመሆን ጉዳዩ እልባት እንዲያገኝ እየሰራን ነው ብለዋል።
ሙስሊም ተማሪዎች ላይ በየጊዜው የሚፈፀሙ የመብት ጥሰቶችን ለማስቆም የጠቅላይ ምክር ቤቱ የትምህርትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኝ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሰራ መሆኑንም አንስተዋል።
- ሀሩን ሚድያ ከጠቅላይ ምክር ቤቱ የትምህርትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ተጠሪ ከሆኑት ከኢንጅነር አንዋር ሙስጠፋ ጋር ያደረግነውን ቆይታ በቀጣይ ወደ እናንተ ምናደርስ ይሆናል።
© ሀሩን ሚድያ