ሶሪያ
አሕመድ አሽ-ሸርዕ(አቡ ሙሐመድ አል-ጁላኒ) የሶሪያ የጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሆኖ ተመርጠዋል።ይህም አዲስ ህገ-መንግስት እስከሚፃፍ ድረስ እንደሚፀና ተገልጿል።
"የሶሪያ አቢዮት ድል ኮንፈረንስ" በሚል በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ እንደተገለፀው ሶሪያ ከ2012 ጀምሮ ስትተዳደርበት የነበረው ህገ-መንግስት መሻሩና የሀገሪቱ ፓርላማና የመከላከያ ተቋማትም አንደተበተኑ በይፋ ታውጇል።በፕሬዚዳንቱ በኩልም አዲስ ጊዜያዊ ህግ አውጪ ምክር ቤት እንደሚቋቋም የተነገረ ሲሆን የወታደራዊ እንቅስቃሴው አስተዳደር ቃል አቀባይ እንደገለፁትም በሀገሪቱ ያሉ የትጥቅ ቡድኖች ሙሉ ለሙሉ ተበትነው አዲስ ሀገራዊ የመከላከያ ተቋም እንደሚገነባ አሳውቀዋል።
አሕመድ ሸርዕ ዛሬ ከሩሲያ ልዑክ ጋር በደማስቆ የተገናኙ ሲሆን፤ሩሲያ በሻር አል-አሰድን አሳልፋ እንድትሰጣቸው ጠይቀዋል።ሩሲያ በበኩሏ ከአዲሱ የሶሪያ መንግስት ጋር በመቀራረብ እንደምትሰራ ገልፃለች።ልዑኩ ስለ በሻር ጉዳይ ግን ምንም ያለው ነገር የለም።
በሰሜን-ምስራቁ ክፍል የሚገኙት የኩርድ ታጣቂዎች እስካሁን ከተሞችን ተቆጣጥረው የሚገኙ ሲሆን፤ለድርድር ዝግጁ መሆናቸውንም አሳውቀዋል።ባለፉት ሳምንታትም በተለያዩ ከተሞች ከአዲሱ አስተዳደር ሰራዊት ጋር ሲፋለሙ ቆይተዋል።
ወራሪዋ እስራኤልም በደቡባዊ ክፍሉ በተቆጣጠረችው ስፍራዎች በርካታ የጦር ካምፖችን የገነባች ሲሆን አዲሱ አስተዳደር እስራኤል የሶሪያን ምድር ለቃ እንድትወጣ ማስጠንቀቂያ እየሰጠ ይገኛል።