"ኡማ ቲቪ " Tv


Гео и язык канала: Иран, Фарси
Категория: не указана


መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+UAKV38o3WF-YJ6jh

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Иран, Фарси
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ቁርኣንን በአደባባይ በማቃጠል የሚታወቀው ኢራቃዊው ክርስቲያን ሰልዋን ሞሚካ በስዊድን በቲክቶክ የቀጥታ ስርጭት ላይ እያለ በተተኮሰበት ጥይት ተገድሏል።
ለተጨማሪ መረጃወቾ ለማገኘት
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+UAKV38o3WF-YJ6jh


አላሁ አክበር!

በ2023 ላይ በስዊድን ጎዳና ላይ የተከበረውን ቁርዓን በማቃጠል ሲሳለቅና ሲረግጥ የነበረው ኢራቃዊው ስደተኛ ሰልማን ሞሚካ በመኖርያ አፓርትመንቱ ውስ ተገደለ።

አላሁ አክበር! አላሁ አክበር

ዜናውን በርካታ ሚዲያወች እየዘገቡት ይገኛሉ። ።ስዊድን ውስጥ ቁርዓንን ማቃጠል በግልፅ የተፈቀደ በመሆኑ የተለያዩ ፅንፈኛ ሙስሊም ጠሎች በየ ጊዜው ሲተገብሩት ጥበቃ ሁሉ ይደረግላቸዋል።

ለተጨማሪ መረጃወቾ ለማገኘት
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+UAKV38o3WF-YJ6jh


ይህ አለም አቀፍ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው። ስብሰባውን እየመሩ ካሉ ሳይንቲስቶች ውስጥ ኒቃብ የለበሰች እህት እያያችሁ ነው። ወዳጆች ተባባሪ ፕሮፌሰር ናት። PhD ያገኘችው ከ University of Oslo ነው። እና አክሱም ላይ ያላችሁ ኋላ ቀሮች ራሳችሁን አለም ጋር አራምዱ። ሴት ልጅ በለበሰችው ልብስ ምክንያት ትምህርት አትማሪ የምትባልበት 10ኛው ክፍለ ዘመን አይደለም።

©Kh abat


የሒጃብ ክልከላዉ ወሎ ኮምቦልቻ ደርሷል

ኒቃብ ለብሳችሁ የምትመጡ ከሆነ ለፈተና እናስገባችሁም መባላቸውን ሙስሊም ተማሪዎች ሰሞኑን መረጃ እየተናገሩ ነበር ።

ኮምቦልቻ የሀይስኩል ሙስሊም ሴት ተማሪዎችን ትናንት ከልክለዋቸዉ ወንዶቹም እነሱ ካልገቡ አንገባም በማለት የትናንቱን ፈተና ለመፈተን ችለዋል። ዛሬ ግን ካላወለቃችሁ አትገቡም ብለዉናል ዱዓ አርጊልኛ ብላኝ ነዉ ልጄ ወደ ትምህርት የሄደችዉ ስትል አንዲት እናት ተናግራለች ።

የአክሱም ሲገርመን ወሎ ላይ ተጀምሮል


ሶሪያ

አሕመድ አሽ-ሸርዕ(አቡ ሙሐመድ አል-ጁላኒ) የሶሪያ የጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሆኖ ተመርጠዋል።ይህም አዲስ ህገ-መንግስት እስከሚፃፍ ድረስ እንደሚፀና ተገልጿል።
"የሶሪያ አቢዮት ድል ኮንፈረንስ" በሚል በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ እንደተገለፀው ሶሪያ ከ2012 ጀምሮ ስትተዳደርበት የነበረው ህገ-መንግስት መሻሩና የሀገሪቱ ፓርላማና የመከላከያ ተቋማትም አንደተበተኑ በይፋ ታውጇል።በፕሬዚዳንቱ በኩልም አዲስ ጊዜያዊ ህግ አውጪ ምክር ቤት እንደሚቋቋም የተነገረ ሲሆን የወታደራዊ እንቅስቃሴው አስተዳደር ቃል አቀባይ እንደገለፁትም በሀገሪቱ ያሉ የትጥቅ ቡድኖች ሙሉ ለሙሉ ተበትነው አዲስ ሀገራዊ የመከላከያ ተቋም እንደሚገነባ አሳውቀዋል።
አሕመድ ሸርዕ ዛሬ ከሩሲያ ልዑክ ጋር በደማስቆ የተገናኙ ሲሆን፤ሩሲያ በሻር አል-አሰድን አሳልፋ እንድትሰጣቸው ጠይቀዋል።ሩሲያ በበኩሏ ከአዲሱ የሶሪያ መንግስት ጋር በመቀራረብ እንደምትሰራ ገልፃለች።ልዑኩ ስለ በሻር ጉዳይ ግን ምንም ያለው ነገር የለም።
በሰሜን-ምስራቁ ክፍል የሚገኙት የኩርድ ታጣቂዎች እስካሁን ከተሞችን ተቆጣጥረው የሚገኙ ሲሆን፤ለድርድር ዝግጁ መሆናቸውንም አሳውቀዋል።ባለፉት ሳምንታትም በተለያዩ ከተሞች ከአዲሱ አስተዳደር ሰራዊት ጋር ሲፋለሙ ቆይተዋል።
ወራሪዋ እስራኤልም በደቡባዊ ክፍሉ በተቆጣጠረችው ስፍራዎች በርካታ የጦር ካምፖችን የገነባች ሲሆን አዲሱ አስተዳደር እስራኤል የሶሪያን ምድር ለቃ እንድትወጣ ማስጠንቀቂያ እየሰጠ ይገኛል።

6.2k 0 5 10 152

30 days until Ramadan!

اللهم بلغنا رمضان


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
የመስጅዱ ኮሚቴም ስሜታቸውን ሲገልፁ አንድ አባታችን በዚህ መስጅድ ዙሪያ ሁለት ጊዜ ደስ አለን ። ለመጀመሪያ ጊዜ የዛሬ አስራ አምስት አመታት አባታችን ሀጂ ሰይዶ አላህ ይዘንለትና መስጅዱን አሰርቶ ቁልፉን ሲሰጠን በጣም ደስ ብሎን ነበር ። ዛሬ ደሞ ሁለተኛው ደስታችን እናንተ ምንጣፉን ገዝታቹህ ሲነጠፍ ስናይ ለአመታት የተሰበረው ልባችን ተጠግኖ ደስ አለን አሉ አልሀምዱሊላህ ።


የነ ዶ/ር ደብረፂዮን ቡድን ህወሐት ሒጃብ የፖለቲካ ቁማር መጫወቻ አድርጎ እየተጠቀመበት እንደሆነ ተረጋገጠ። ቡድኑ በአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሒጃብ ክልከላ አስመልክቶ እንደተነገረው የእስልምና ጉዳዮች ተወካዮች ከሰልፉ በኋላ ወደ ጊዚያዊ አስተዳደሩ አቶ ጌታቸው እንደሄዱ ለምን ወደኛ አልመጡም። እኛ ጋር ቢመጡ ጉዳያቸው ይፈታላቸው ነበር። አሁኑም ጉዳያቸውን ይፈታላቸው ዘንድ ሚዲያ ላይ ቀርበው ጉዳያችን የሚፈታልን የነ ዶ/ር ደብረፅዮኑ ሕወሓት ነው ብለው መናገር አለባቸው ሲሉ መናገራቸውን ተሰማ።

እኛም እንላለን እጃችሁ ከሒጃብ አንሱ! ሒጃብ መብት እንጂ የፖለቲካ ቁማር መጨዋቻ አይደለም። ሒጃባ ክትገብር እያ ትምህርታ እውን ክትማሃር እያ።


ምን ሁነን ነው ግን?

ትዝ ይላችኋል የዛሬ 3 አመት በፊት may 2022 …የመጀመሪያው አለማቀፍ የቁርዓን ውድድሩ በስታዲየም እንዳይደረግ የተከለከለ ጊዜ? ሰው ያን ሁሉ ትኬት ገዝቶ ገዝቶ… ትዝ ይላችኋል? የቢላልን ሀገር የነጃሺን ሀገር ለአለም ሙስሊሞች እናሳይበታለን ያልነው የቁርዓን ውድድር እሁድ ቀን ተሰርዞ በብዙ ትግል ሰኞ እለት በስታዲየም ተፈቅዶ… ህዝቡ ሰኞ ነው የስራ ቀን ነው አይመጣም ተብሎ ስታዲየም የሞላው ነገርስ… ከተለያየ የሀገሪቱ ክፍል አዳር ተጉዘን አዲስ አበባ የገባነው ነገር… ። ያ የስታዲየም ተክቢራ እንዴት ይረሳል? ተው ስንባል ስንከለከል እልህ አለብን። መብታችን የተነካ መስሎ ሲሰማን ቀጥ ብለን እንቆም ነበር እኮ… ። ዛሬ ላይ የቁርዓን ውድድር መጀመሩን ስሰማ… ያ አጋጣሚ ትዝ አለኝ። ያ ስሜት ግን አሁን አለ? ዛሬም እህቶቻችን ከትምህርት ለማግለል እየተሰራ ባለው በደል ላይ ያ ስሜት ቢኖር ብዬ ተመኘው። እህቶቻችን የክፍል ጓደኞቻቸው ማጠቃለያ ፈተና ተፈትነው እየጨረሱ እነሱ በእምነታቸው ምክንያት ተገፍተው ወደኋላ ሲቀሩ እንደማየት ምን የሚያም ነገር አለ? ምን ሁነን ነው ግን?


VICTORIOUS DECOR AND PASTRIES

ሰላም ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች መጥፋታችንን ይቅርታ እየጠየቅን በትእግስት ከቻናሉ ሳትወጡ ለጠበቃቹን ቤተሰቦች ከልብ እያመሰገንን ለናንተ ድንቅ የሆነ የምስራች ይዘንላቹ መተናል

📢📢📢📢👇👇👇👇👇👇👇

👉 የሰርግ ዲኮር እና ሙሉ የተፈጥሮ አበባ ስልጠና ለመስጠት ዝግጅታችንን ጨርሰናል

👉 ቀድመው ለሚመዘገቡ 10 ሰዎች ማንኛውም አይነት ፕርግራም ቢኖርቦት የጣፋጭ አገልግሎት በነፃ እንሰጣለን

👉 ለቤት እመቤቶች 10% ቅናሽ እናደርጋለን ይህ ማስታወቂያ ከወጣ እስከ 10 ቀን ባለው ውስጥ ከተመዘገቡ

👉 እኛ ጋር ተምረው ወደ ስራው አለም ስትቀላቀሉ ሙሉ የዲኮር እቃ ኪራይ በአነስተኛ ዋጋ ያገኛሉ

👉 የምንቀበለው 60 ተማሪዎችን ብቻ ነው

👉 ስልጠናው ለ አንድ ወር ከ ሳምንት የሚቆይ ነው

👉 ለ አጭር ግዜ የሚቆይ ቅናሽ ነው በ 8000 ብር ብቻ ነው የምናስተምረው

👉 አድራሻችን ወሎ ሰፈር ድሬ ዳዋ ህንፃ ፊት ለፊት የሚገኘው አብዲሳ መኪና መሸጫ ውስጥ

👉 ለበለጠ መረጃ 0911267699 በስራ ሰአት ይደውሉልን

👉 በማንኛውም ሰአት በቴሌግራም ያዋሩን @victoriousdecor

የቴሌግራም ገፅ https://t.me/+BKJ-K87eh3QxMGI0

የቲክ ቶክ ገፅ https://www.tiktok.com/@victoriousdecorr?_t=ZM-8tJNfXbg3YT&_r=1

👉 ቲክ ቶክ ላይም ፎሎ በማድረግ በየጊዜው የሚወጡ ነፃ እድሎችን ያግኙ


ኡስታዝ አቡበከር አህመድና ኡስታዝ ያሲን ኑሩ የሀሩን ሚድያን የአዲስ አበባ ስቱድዮን ጉበኙ

- ሀሩን ሚዲያ፥ ጥር 21/2017

በዳዕዋ ስራዎቻቸውና በሙስሊሙ ማኅበረሰብ አወንታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ በስፋት በመሳተፍ የሚታወቁት ኡስታዝ አቡበከር አህመድና ኡስታዝ ያሲን ኑሩ የሀሩን ሚድያ አዲስ አበባ ስቱድዮን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸው ወቅታም ሀሩን ሚዲያ ላለፉት ሰባት ዓመታት በሚዲያው ዘርፍ እየሰራቸው ያሉትን ስራዎች አስመልክቶ በሚድያው የአዲስ አበባ ስቱድዮ ስራ አስኪያጅ አቶ ባህሩ አባስ አማካኝነት ገለፃ ተደርጎላቸዋል።

ኡስታዞቹ በመልዕክታቸውም ሀሩን ሚድያ የሙስሊሙ ማህበረሰብ የመረጃ ክፍተት በመሙላት እየሰራ ያለውን ስራ አድንቀው ሙስሊሙ ማህበረሰብ ሚድያውን በተለያየ መንገድ እንዲያጠናክር ጥሪ አቅርበዋል።

© ሀሩን ሚድያ


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
የረመዳን አስቬዛ

ከ ሀገር ውጭ የሚገኙ የአማና ማርኬት እና ዴሊቨሪ ቤተሰቦች ለረመዳን አስቬዛ ለወዳጅ ዘመዶ ከኛ ሲሸምቱ ተጨማሪ ሀዲያወችን/ስጦታወች ያግኙ

            የዎጋ ዝርዝር ና የምንሰጣቸውን
                    አገልግሎት ለማወቅ


#በቴሌግራም
#በዋትስአፕ
#ኢንስታግራም
#ቲክቶክ
#በኢሞ እና በተለያዬ የሶሻል ሚዲያ አማራጮች ያግኙን

ስልክ ቁጥር :-0933267711
                :-0930950531
                :-0991119303

የቴሌግራም ሊንክ
@amana_market
@amana_market1
@amana_market2
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/amana_markett
የቲክቶክ ሊንክ
tiktok.com/@amana_market


2ኛው አለም አቀፍ የቁርአን እና የአዛን ውድድር የማጣሪያ ውድድር!

ቀጥታ ስርጭት ከአዲስአበባ

https://www.facebook.com/haruntube/videos/1758213854960067/?app=fbl


ሆስፒታሎች እና መስጂዶችን ጨምሮ በጋዛ የወደሙ መሠረተ ልማቶችን ሀገራቸው እንደምትገነባ የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር ተናገሩ

የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም፤ በእስራኤል ጥቃት በጋዛ የወደሙ ሆስፒታሎችን፣ ትምህርት ቤት እና መስጂዶችን ሀገራቸው እንደምትገነባ በዛሬው እለት ተናግረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን በኤክስ ገጻቸው ላይ ያሳወቁት በጋዛ ተኩስ አቁም ተደርጎ ነዋሪዎች መመለስ ከጀመሩ በኋላ ነው፡፡

የተኩስ አቁም ተግባራዊ መደረጉን ጋዛን ለመገንባት እንደ ጥሩ አጋጣሚ መጠቀም እንደሚገባ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር፤ በጥቃቱ ከ46 ሺሕ በላይ ንጹሐን መገደላቸውን እንዲሁም ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለመፈናቀል መገደዳቸውንም አስታውሰዋል፡፡ አያይዘውም የደረሰውን ጉዳት ለመጠገን ሀገራቸው እገዛ እንደምታደርግ አስታውቀዋል፡፡

ፍልስጤም ነጻ ሀገር መሆን አለባት በሚል በሚያራምዱት አቋም የሚታወቁት የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር፤ ከአስር ቀናት በፊት የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት “ለነጻ የፍልስጤም መንግሥት ምሥረታ እንደ አንድ ርምጃ ማገልገል አለበት” ብለው ነበር።

በወቅቱ ንግግራቸው፤ በተመሳሳይ በጋዛ “የተደረገውን የተኩስ አቁም በደስታ የምንቀበል ቢሆንም በአስር ሺሕዎች የሚቆጠሩ የፍልስጤም ንጹሐን ሕይወት መቀጠፉ እንዲሁም ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው” ሊረሳ እንደማይችል ገልጸው ነበር፡፡ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የተኩስ አቁሙ ዘላቂ እንዲሆን ጫና ማድረግ እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

በሐማስ እና እስራኤል መካከል የተደረሰው የጋዛ ተኩስ አቁም በሦስት ደረጃ ተፈጻሚ እንደሚደረግ በአንደኛዋ አደራዳሪ ኳታር መገለጹ የሚታወስ ነው፡፡


"ህጋዊ ካርታ ያለው መስጂድ በ5 ቀናት ውስጥ እንዲፈርስ ትዕዛዝ ተሰጥቶብናል!"

- የለገጣፎ ለገዳዲ መጅሊስና የሱመያ መስጂድ ኮሚቴዎች

ሀሩን ሚድያ፣ ጥር 21/2017

በሸገር ከተማ በለገጣፎ ለገዳዲ ክፍለከተማ ህጋዊ ካርታ ያለው ሱመያ መስጂድ በፍርድ ቤት እንዲነሳ ያለአግባብ ውሳኔ መሰጠቱን አስመልክቶ ሀሩን ሚድያ ህዳር 19/2017 ዓ.ል በቦታው በመገኘት ዘገባ መስራታችን ይታወሳል።

አሁንስ የመስጂዱ ጉዳይ ከምን ደረሰ ብለን የሱመያ መስጂድ ኮሚቴዎችን እና የለገጣፎ ለገዳዲ ክፍለከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ጠይቀናል።

ኮሚቴዎቹ በሰጡን ምላሽ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ በፍርድ ቤት በኩል ለለገጣፎ ለገዳዲ ክፍለከተማ አስተዳደር እንደተሰጠውና መስጂዱን እስከ ጥር 26/2017 እንዲያፈርስ ትዕዛዝ መሰጠቱን ተነግሯናል ብለዋል።

የለገጣፎ ለገዳዲ መጅሊስ ከሸገር ከተማ መጅሊስ ጋር በመሆን ይህ ኢ-ፍትሀዊ የሆነ ውሳኔ መላውን የሙስሊም ማህበረሰብ ያስቆጣ ጉዳይ በመሆኑ የፀጥታ ችግር መንስኤ እንዳይሆን አስተዳደራዊ ውሳኔ እንዲሰጣቸው በተደጋጋሚ ቢጠይቁም የሸገር ከተማ አስተዳደር ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄ ምላሽ መስጠት አለመቻሉን በምሬት ገልፀዋል።

በሸገር ከተማ በለገጠፎ ለገዳዲ በደንበል ጣፎ ከ2002 ዓ.ል ጀምሮ የአካባቢው ነዋሪዎች አካባቢው ላይ ምንም አይነት መስጂድ ባለመኖሩ ጥያቄያቸውን የጀመሩ መሆኑን በማንሳት ከዛም ነሀሴ 2014 ዓ.ል በዒድ ቀን በከተማ አስተዳደሩ 2077 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ የሱመያ መስጂድ ህጋዊ ካርታ እንደተሰጣቸው ገልፀዋል።

የተሰጣቸው ቦታ ቆሻሻ መጣያ ስለነበር እሱን በማፅዳት መስጂድ በመገንባት ሲገለገሉበት ቆይተው አካባቢው ላይ ባሉ አንዳንድ አካላት መስጂዱ እንዲነሳ ጥያቄ ቢያቀርቡም የከተማ አስተዳደሩ እንዳልተቀብላቸው ተገልጿል።

በ2001 ካሳ የወሰደ አርሶ አደር መስጂዱ በጉልበት 1,000 ካሬ ሜትር ወስዶብኛል በሚል ክስ መስርቷል። ፍርድ ቤት በነበረው ክርክርም የመስጂዱ ካርታ ህጋዊ መሆኑንና ለገበሬው ካሳ መከፈሉን በማስረጃ ቢያቀርቡም ፍርድ ቤቱ መስጂዱ እንዲነሳ በሚል ያለአግባብ ውሳኔ መወሰኑን የመስጂዱ ኮሚቴዎች ተናግረዋል።

የመስጂድ ጉዳይ የህዝብ በመሆኑ መስጂዱን በተመለከተ አሁንም የሚመለከተው የሸገር ከተማ መስተዳደር አስተዳደራዊ ውሳኔ ይሰጠን ሲሉ የለገጣፎ ለገዳዲ ክፍለከተማ መጅሊስና የመስጂዱ ኮሚቴዎች ጠይቀዋል።

© ሀሩን ሚድያ




የ2ኛው አለም አቀፍ የቁርአን እና የአዛን ውድድር የመክፈቻ ስነ ስርዓትና የማጣሪያ ውድድር እየተካሄደ ይገኛል!

በዘይድ ኢብኑ ሳቢት የቁርአን ማህበር አዘጋጅነት በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የበላይ ጠባቂነት በመጭው እሁድ በአዲስአበባ ስታዲየም የሚካሄደው ሁለተኛው አለም አቀፍ የቁርአን እና አዛን ውድድር የመክፈቻ ስነ ስርዓትና የማጣሪያ ውድድር በዛሬው ዕለት በኢሊሌ ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል።

የማጣሪያ ውድድሩ ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ60 የተለያዩ ሀገራቶች የመጡ ተወዳዳሪዎች የሚሳተፉበት ሲሆን የዛሬውን የማጣሪያ ውድድር ያለፉ ተወዳዳሪዎች በመጭው እሁድ በአዲስአበባ ስታዲየም የፍፃሜ ውድድር ተፋላሚ እንደሚሆኑ ተገልጿል።

በዛሬው ዕለት በኢሊሌ ሆቴል እየተካሄደ በሚገኘው የማጣሪያ ውድድር የመክፈቻ ዝግጅት ላይ የፌዴራል እና የአዲስአበባ መጅሊስ አመራሮች ፣ አለምአቀፍ የቁርአን ውድድር ዳኞች ፣ ከተለያዩ ሀገራት የተጋበዙ ሊቃውንት ፣ኡለማኦች ኡስታዞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

Показано 17 последних публикаций.