ምን ሁነን ነው ግን?
ትዝ ይላችኋል የዛሬ 3 አመት በፊት may 2022 …የመጀመሪያው አለማቀፍ የቁርዓን ውድድሩ በስታዲየም እንዳይደረግ የተከለከለ ጊዜ? ሰው ያን ሁሉ ትኬት ገዝቶ ገዝቶ… ትዝ ይላችኋል? የቢላልን ሀገር የነጃሺን ሀገር ለአለም ሙስሊሞች እናሳይበታለን ያልነው የቁርዓን ውድድር እሁድ ቀን ተሰርዞ በብዙ ትግል ሰኞ እለት በስታዲየም ተፈቅዶ… ህዝቡ ሰኞ ነው የስራ ቀን ነው አይመጣም ተብሎ ስታዲየም የሞላው ነገርስ… ከተለያየ የሀገሪቱ ክፍል አዳር ተጉዘን አዲስ አበባ የገባነው ነገር… ። ያ የስታዲየም ተክቢራ እንዴት ይረሳል? ተው ስንባል ስንከለከል እልህ አለብን። መብታችን የተነካ መስሎ ሲሰማን ቀጥ ብለን እንቆም ነበር እኮ… ። ዛሬ ላይ የቁርዓን ውድድር መጀመሩን ስሰማ… ያ አጋጣሚ ትዝ አለኝ። ያ ስሜት ግን አሁን አለ? ዛሬም እህቶቻችን ከትምህርት ለማግለል እየተሰራ ባለው በደል ላይ ያ ስሜት ቢኖር ብዬ ተመኘው። እህቶቻችን የክፍል ጓደኞቻቸው ማጠቃለያ ፈተና ተፈትነው እየጨረሱ እነሱ በእምነታቸው ምክንያት ተገፍተው ወደኋላ ሲቀሩ እንደማየት ምን የሚያም ነገር አለ? ምን ሁነን ነው ግን?