ሆስፒታሎች እና መስጂዶችን ጨምሮ በጋዛ የወደሙ መሠረተ ልማቶችን ሀገራቸው እንደምትገነባ የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር ተናገሩ
የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም፤ በእስራኤል ጥቃት በጋዛ የወደሙ ሆስፒታሎችን፣ ትምህርት ቤት እና መስጂዶችን ሀገራቸው እንደምትገነባ በዛሬው እለት ተናግረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን በኤክስ ገጻቸው ላይ ያሳወቁት በጋዛ ተኩስ አቁም ተደርጎ ነዋሪዎች መመለስ ከጀመሩ በኋላ ነው፡፡
የተኩስ አቁም ተግባራዊ መደረጉን ጋዛን ለመገንባት እንደ ጥሩ አጋጣሚ መጠቀም እንደሚገባ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር፤ በጥቃቱ ከ46 ሺሕ በላይ ንጹሐን መገደላቸውን እንዲሁም ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለመፈናቀል መገደዳቸውንም አስታውሰዋል፡፡ አያይዘውም የደረሰውን ጉዳት ለመጠገን ሀገራቸው እገዛ እንደምታደርግ አስታውቀዋል፡፡
ፍልስጤም ነጻ ሀገር መሆን አለባት በሚል በሚያራምዱት አቋም የሚታወቁት የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር፤ ከአስር ቀናት በፊት የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት “ለነጻ የፍልስጤም መንግሥት ምሥረታ እንደ አንድ ርምጃ ማገልገል አለበት” ብለው ነበር።
በወቅቱ ንግግራቸው፤ በተመሳሳይ በጋዛ “የተደረገውን የተኩስ አቁም በደስታ የምንቀበል ቢሆንም በአስር ሺሕዎች የሚቆጠሩ የፍልስጤም ንጹሐን ሕይወት መቀጠፉ እንዲሁም ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው” ሊረሳ እንደማይችል ገልጸው ነበር፡፡ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የተኩስ አቁሙ ዘላቂ እንዲሆን ጫና ማድረግ እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡
በሐማስ እና እስራኤል መካከል የተደረሰው የጋዛ ተኩስ አቁም በሦስት ደረጃ ተፈጻሚ እንደሚደረግ በአንደኛዋ አደራዳሪ ኳታር መገለጹ የሚታወስ ነው፡፡