የ2ኛው አለም አቀፍ የቁርአን እና የአዛን ውድድር የመክፈቻ ስነ ስርዓትና የማጣሪያ ውድድር እየተካሄደ ይገኛል!
በዘይድ ኢብኑ ሳቢት የቁርአን ማህበር አዘጋጅነት በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የበላይ ጠባቂነት በመጭው እሁድ በአዲስአበባ ስታዲየም የሚካሄደው ሁለተኛው አለም አቀፍ የቁርአን እና አዛን ውድድር የመክፈቻ ስነ ስርዓትና የማጣሪያ ውድድር በዛሬው ዕለት በኢሊሌ ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል።
የማጣሪያ ውድድሩ ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ60 የተለያዩ ሀገራቶች የመጡ ተወዳዳሪዎች የሚሳተፉበት ሲሆን የዛሬውን የማጣሪያ ውድድር ያለፉ ተወዳዳሪዎች በመጭው እሁድ በአዲስአበባ ስታዲየም የፍፃሜ ውድድር ተፋላሚ እንደሚሆኑ ተገልጿል።
በዛሬው ዕለት በኢሊሌ ሆቴል እየተካሄደ በሚገኘው የማጣሪያ ውድድር የመክፈቻ ዝግጅት ላይ የፌዴራል እና የአዲስአበባ መጅሊስ አመራሮች ፣ አለምአቀፍ የቁርአን ውድድር ዳኞች ፣ ከተለያዩ ሀገራት የተጋበዙ ሊቃውንት ፣ኡለማኦች ኡስታዞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።