በማንነት ቀውስ የጦዘ ማንነት
“ጥላቻና መራራነት ማለት አንዲትን አይጥ ለመግደል ቤትህን በእሳት ማቃጠል ማለት ነው” - Henry Fosdick
የአዶልፍ ሂትለር ታላቅ ወንድም የአባቱ ጨካኝነትን ለማምለጥ በ13 አመቱ ነበር ከቤቱ በርሮ የጠፋው፡፡ ይህ ልጅ ከቤቱ ከሄደ በኋላ የሂትለር አባት ክፋቱን በሰባት አመቱ ለጋ ልጅ በሂትለር ላይ በእጥፍ ጨመረው፡፡ ሂትለር በአባቱ እጅ አሰቃቂ አመታትን አልፏል፡፡ ምርጫውን ተከልክሎአል፡፡ አርቲስት ለመሆን ይመኝ የነበረው ሂትለር በአባቱ አስገዳጅነት የሲቪል ሰራተኛነት አቅጣጫን እንዲከተል ተገደደ፡፡ የሂትለር ትምህርት ውጤቱ አጥጋቢ ስላልነበር የአባቱን የቁጣ እጅግ አባባሰው፡፡ የአይሁድ ዘር እንዳለበት የሚነገረው የሂትለር አባት ክፋት በሂትለር ልብ ውስጥ አይሁድን የመጥላት ዘርም እንደዘራበት ይነገራል፡፡
አባቱ ከሞተ በኋላ፣ ሂትለር በ13 አመቱ የቤት ሃላፊትን በጫንቃው ላይ ተሸከመ፡፡ በእናቱ ሞት ምክንያት በኋላ በጉዲፈቻ ያድግ የነበረው ሂትለር ያንን ገቢ በመከልከሉ የጎዳናን ሕይወት ቀምሷል፡፡ በብዙዎች እንደሚታመነው፣ ሂትለር በልጅነቱ ያሳለፈው ስቃይ ውስጡ ከጨመረበት መራራነት እንዳልተላቀቀና በሕይወቱ ያደረጋቸው አሰቃቂ ተግባሮች የዚያ ልምምድ ተጽእኖ እንደሆኑ ይታመናል፡፡ ሂትለር ቢያንስ ለ46 ሚልየን ሰዎች መሞትና ለብዙ ንብረት መውደም ምክንያት የሆነ ሰው ነው፡፡ ሂትለር የዚህ ሁሉ ውደመት ምክንያት ከሆነ በኋላ ራሱን በራሱ አጥፍቶ እስኪሞት ድረስ ይህንን እብደቱን የሚከተሉለት ከእርሱ የባሱ እብዶች ፈጽሞ አጥቶ አያውቅም ነበር፡፡
አንዳንድ ሰዎች ምንም እንኳን በተለያዩ ለማንነት ቀውስ (Identity Crisis) አሳልፈው በሚሰጡ ልምምዶች ውስጥ አልፈው ቢያድጉም፣ ከዚያ ሁኔታ በተሳካ መልኩ ራሳቸውን አውጥተው ለሕብረተሰቡ ጠቃሚ ዜጎች ይሆናሉ፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች ብዙዎችን ወደ አንድነት፣ ወደመከባበርና ወደ አብሮነት የሚያመጡ የመልካም ተጽእኖ ሰዎች ናቸው፡፡
አንዳንዶች ግን በመራራነት፣ በጥላቻና በአስተዳደግ ዘመናቸው በተጎነጩት የውስጥ ቂም የተቃወሰ ማንነት ይዘው ወደ አመራር ይዘልቃሉ - እንዴት አይነት ስህተት! እንደዚህ አይነት ሰዎች በውስጣቸው ያለባቸው የማንነት ቀውስ ይህ ነው ተብሎ ሊተነበይ የማይችልን ባህሪይ እንዲገልጡ ይነዳቸዋል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የተጠናወታቸው የተቀባይነት ጥማትና የደጋፊ ፍለጋ ናፍቆት ምንም ነገር ከማድረግ እንዳይመለሱ አይኖቻቸውን አሳውሯቸዋል፡፡
እውነቱ አጭርና ግልጽ ነው፡- ካለፈው ሕይወት ተጽእኖ በስኬታማ ሁኔታ ራሱን መርቶ ያላወጣ ሰው ሌላውን ለመምራት ሲሞክር ሊያስከትለው የሚችለው ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡ ማንነቱንና ምንነቱን በሚገባ ሳይገነዘብና ሳይቀበል ያደገ ሰው ከዚያ የማንነት ቀውስ ነጻ ካልወጣ በስተቀር የራሱንና የሕብረተሰቡን ጤንነት እንዳወከ ይኖራል፡፡ እንደዚህ አይነቱ ሰው ብዙ ሳይቆይ ከመዘዝ አያመልጥም፡፡
በቅንነት ሼር ያድርጉልኝ 👇
http://t.me/psychologypages