አስተዳደጌ !!!
የመጀመሪያዎቹ አምስት አመታቶቻችን (Formative age) ወደፊት በዙሪያችንና በሕይታችን ላይ ያለንን ንጽረተ-ዓለም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የመቅረጽ ጉልበት አላቸው ይባላል፡፡ በለጋነት እድሜያችን ያሳለፍናቸውን የአስተዳደግ ሁኔታዎች መለስ ብሎ ማየትና መገንዘብ አስፈላጊ ነው፡፡ የአስተዳደግን ሁኔታ ማወቅ ማለት ባደግንበት ቤት ውስጥ ምን አይነት “መንፈስ” ጠጥተን እንዳደግን መለየት ማለት ነው፡፡ በልጅነትህ ስታየውና ስትሰማው ያደከው ሁኔታ በአንተ ላይ ታላቅ የሆነ ተጽእኖ አለው፡፡ በተለይ ከወላጅ ቤተሰቦችህ ወይም ካሳደጉህ ሰዎች ጋር ያሳለፍካቸው የለጋነት ዘመኖችህ በማንነትህ ላይ ትልቅ ስፍራ አላቸው፡፡
በሃገራችን ውስጥ ብዙ ሰዎች የልጅነት ትዝታቸውን ማሰብ አይፈልጉም፡፡ ያን ጊዜ የደረሰባቸው፣ የሆኑትና እያዩ ያደጉት ሁኔታ በአእሮአቸው ውስጥ ተጋግሮ ማድረግና መሆን የሚችሉት ነገር ላይ ገደብ ጥሎባቸዋል፡፡ ከዚህ ሁኔታ አልፎ ለመሄድ ግን ቁርጥ ውሳኔንና እርምጃን የሚጠይቅ ጉዳይ ነው፡፡
የአስተዳደግህን ሁኔታ ለማወቅ የሚከተሉትን ነጥቦች ማሰብ ትችላለህ፡-
1. ቤተሰቦቼ ከእኔ ጋር
ቤተሰቦቼ በግሌ ምን ሲነግሩኝ፣ ምን ሲያደርጉልኝ ወይም ሲያደርጉብኝ አደግሁ? ቤተሰቦቼ ከእኔ ጋር የነበራቸው ግንኙነት በዙሪያዬ ባለው አለም ላይ ለሚኖረኝ አመለካከት ታላቅ ተጽአኖ አለው፡፡ ስለዚህ ምናልባት አሁን ያለኝ የስሜትም ሆነ የአመለካከት ቀውስ ከዚያ ይገናን እንደሆነ በማሰብ ተገቢውን የእርማት እርመጃ መውሰድ ሊያስፈልገኝ ይችላል፡፡
2. ቤተሰቦቼ እርስ በርሳቸው
ቤተሰቦቼ እርስ በርሳቸው በምን ሁኔታ ሲስተናገዱ አይቼ አደግሁ? ወላጆቼ እርስ በርሳቸው ሲከባበሩ አይቼ አደኩ ወይስ ሲበዳደሉ? ይህ ሁኔታ በወደፊቴ ላይ አሉታዊ ወይም አዎንታዊ ስፍራ አለው፡፡ ከዚህ አይነቱ ተጽእኖ ነጻ ያልዉ ሰዎች በወደፊት ባላቸው የፍቅር ግንኙነት ላይ ይህ ነው የማይባል ጫና ሊኖርባቸው ይችላል፡፡
3. ቤተሰቦቼ ከኑሮአቸው ጋር
ቤተሰቦቼ የኑሮን ተግዳሮትም ሆነ በረከት በምን መልኩ ሲያስተናግዱ አይቼ አደግሁ? ወላጆቼ ችግር ሲጋፋቸውም ሆነ ምቾት ሲመጣ ይሰጡት ለእነዚህ አይቀሬ የሕይወት ክስተቶች የነበራቸው ምላሽ በእይታዬ ላይ ወሳኝ የሆነን ነገር ይቀርጻል፡፡ በሕይወት ዘመናችን አንዳንዴ በችግር ሌላ ጊዜ ደግሞ በምቾት እናልፋለን፡፡ እነዚህን የኑሮ “ፍርርቆች” አያያዜ የወደፊቴን መወሰኑ አይቀርም፡፡
አይህ …
• ልጅ ጥላቻ በሞላበት አካባቢ ካደገ፣ ጸበኝነትን ይማራል፡፡
• ልጅ ሃፍረት በነገሰበት አካባቢ ካደገ፣ የጥፋተኝነት ስሜትን ይማራል፡፡
• ልጅ ምስጋና በተለመደበት አካባቢ ካደገ፣ ሰዎችን ማድነቅና ማመስገን ይማራል፡፡
• ልጅ በሚያበረታታ አካባቢ ካደገ፣ ድፍረትን ይማራል፡፡
• ልጅ አንድ ሰው ሌላውን በሚገነዘብበት አካበቢ ካደገ፣ ትእግስትን ይማራል፡፡
• ልጅ እውነተኛ ፍርድ ባለበት አካባቢ ካደገ፣ ፍትሃዊነትን ይማራል፡፡
• ልጅ ከአደጋ ነጻ በሆነ አካባቢ ካደገ፣ መታመንን ይማራል፡፡
• ልጅ ድጋፍን በሚያገኝበት አካባቢ ካደገ፣ በራስ መተማመንን ይማራል፡፡
• ልጅ ተቀባይነትና ጓደኝነት ባለበት አካባቢ ካደገ፣ በሰዎች ውስጥ ፍቅርን ማየትን ይማራል
በቅንነት ሼር ያድርጉልኝ 👇
http://t.me/psychologypages