በቂም የተቆለፈ ልብ
ሰሞኑን ይቅርታ የመጠየቅን አስፈላጊነት በመጠኑ ተመልክተናል፡፡ የዚህን ሃሳብ ግልባጭ፣ ማለትም፣ ይቅርታ የማድረግን ገጽታ አስመልክቶ ጥቂት እንመለክት፡፡ አንድ ስህተተኛ ወገን ይቅርታን ለመጠየቅ ራሱን ሲያቀርብ ተበዳይ ወገን ይቅርታውን ለመቀበል የተዘጋጀ ልቦና ያስፈልገዋል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ለደረሰባቸው በደል ምንም አይነት የይቅርታ መልእክት ቢሰጣቸው እንኳ ንቅንቅ ያለማለትና ልባቸውን “በቂም ቁልፍ” የመቆለፍ ዝንባሌ አላቸው፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ በሕይወታቸው ይህ ነው የማይባልን ድርብ ቁስል ያመጣባቸዋል፡፡
በሰዎች በደረሰባቸው በደል በመቁሰላቸው ምክንያት ቂም የያዙ ሰዎች ራሳቸውን እንደገና የሚያቆስሉ ሰዎች ናቸው፡፡ ይህ እንዳይሆን ይህንን አይነት ዝንባሌ እንዲያዳብሩ የዳረጓቸውን አንዳንድ ቅድመ-ሁኔታዎች መገንዘብ አስፈላጊ ነው፡
የግንኙነቱ ሁኔታ
አንድ ከዚህ በፊት በፍጹም የማናውቀው ሰው በአጋጣሚ ሲበድለን ሊኖረን የሚችለው የመጎዳት ሁኔታና የብዙ ዘመን ወዳጅነት፣ ቤተሰብነት ወይም የፍቅር ጓደኝነት ውስጥ አብሮን የቆየ ሰው ሲበድለን በስሜታችን ላይ ያለው ጫና ይለያያል፡፡ ሆኖም፣ ሁኔታው ምንም ከባድ ቢሆን ያንን ለማለፍ የስሜትን ብልህነት ማዳበር ተገቢ ነው፡፡
የጥፋቱ ጥልቀት
አንድ ሰው የሰራው ስህተት የጠለቀ ሲሆንና በስሜታችን፣ በስነ-ልቦናችን፣ በኢኮኖሚያችንም ሆነ በአካላችን ላይ ያደረሰው ጉዳት ጠንካራ ሲሆን ከይቅርታ ይልቅ ይቅር አለማለት ሊያመዝንብን ይችላል፡፡ ሆኖም፣ ቂም የተያዘበት ሰው ከሚደርስበት የስሜት ጫና ይልቅ የከፋው ጫናና የስሜት ቀውስ ያለው ቂም የያዘው ሰው ላይ የመሆኑን እውነታ ልምምድም ሆነ ሳይንስ ያረጋግጡልናል፡፡ ስለዚህም፣ በጉዳዩም ተጎድተን፣ ይቅር ባለማለትም ራሳችንን ጎድተን ድርብህመም ውስጥ ከመግባት የይቅርታን መንገድ መምረጡ አስፈላጊ ነው፡፡
የጥፋቱ ተደጋጋሚነት
አንዴ ለበደለን ሰው ይቅርታ ማድረግ ሊቀል ይችላል፡፡ ሆኖም፣ ይኸው ሰው ደጋግሞ ሲበድለን በሰውየው ላይ ያለን አመለካከት እየተበላሸ ሊሄድ ሰለሚችል ለይቅርታ ያለንን ፈቃደኝነት ይነካዋል፡፡ ሆኖም፣ ይህ ሰው ከዚህ በኋላ ደጋግሞ እንዳይጎዳን ለወደፊቱ በጥበብ የመቅረብን ሁኔታ ማዳበር አለብን እንጂ ልቦናችንን ከይቅርታ መዝጋት የለብንም፡፡ ደጋግሞ የጎዳን ሰው እኮ እኛው ደጋግመን በማመናችን ምክንያት ነው፡፡ ደጋግሞ ማመን ችግር ባይኖረውም፣ “በጥበብ ማመን” የሚባል ነገር እንዳለ ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡
በደሉ የተፈጸመበት “መንፈስ”
አንድን ስህተት የሰራ ሰው ያንን ስህተት የሰራው ቅድመ-ዝግጅትን አድርጎ፣ በሚገባ አስቦበትና በተንኮል ሲሆን በተበዳዩ ላይ የሚያመጣው ጉዳት ጠንከር ይላል፡፡ በተቃራኒው ሰዎች በስህተት የሰሩት በደል በተበዳዩ ላይ የመለስለስ ዝንባሌን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ይቅርታ ግን ሁለቱንም የበደል አይነቶች አልፎ ሊሄድ የሚችል ጉልበት አለው፡፡ አስቦበትና አድፍጦ የበደለህንና የጎዳህን ሰው በልብህ ይቅር በለው፣ ለወደፊቱ ግን ትምህርትን አግኝና ራስህን ጠብቅ፡፡
በቅንነት ሼር ያድርጉልኝ 👇
http://t.me/psychologypages