ቅዱስ ቁርኣንን ወደ ቋንቋዋ ለመመለስ የተዘጋጀችው ሀገር
ቅዱስ ቁርኣን ከወረደበት የዐረቢኛ ቋንቋ፤ አማርኛን ጨምሮ ወደተለያዩ የዓለም ቋንቋዎች ተተርጉሞ ይገኛል። የቁርኣን የተመረጡ አንቀፆች እስካሁን ድረስ ወደ 114 ቋንቋዎች የተተረጎመ ሲሆን፣ ሙሉ ቃሉ የተመለሰው ደግሞ ወደ 47 ቋንቋዎች ነው።
በዚህ ሳምንት ደግሞ የሰሜን አፍሪካዋ ሀገር ሞሮኮ፣ በሀገሯ ወደሚነገር ቋንቋ የመተርጎም እቅድ መያዟን ይፋ አድርጋለች። የሀገሪቱ የእስልምና ጉዳዮች ሚኒስቴር እንዳሳወቀው ከሆነ፣ የቁርኣንን ሙሉ ቃል ወደ አማዚግ ቋንቋ ለመመለስ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።
አማዚግ የተሰኘው ቋንቋ እ.አ.አ ከ2011 አንስቶ የሞሮኮ ይፋዊ ቋንቋ በመሆን እያገለገለ ነው። ተማዚግት በሚል ተለዋጭ መጠሪያ የሚታወቀው ይህ ቋንቋ፣ ከአፍሮ ኤዥያቲክ ቋንቋ ቤተሰብ የሚመደብ ነው። ከ30 በመቶ በላይ በሚሆኑ ሞሮካዊያንም ይነገራል።
በኢትዮጵያ ወደ አማርኛ ቋንቋ የተተረጎመው ቅዱስ ቁርኣን ለኅትመት የበቃው በ1961 ነው። ትርጉሙ የተሠራው በሐጂ ሙሐመድ ሣኒ ሐቢብ እና ሸይኽ ሰይድ ሙሐመድ ሳዲቅ መሆኑ ይታወቃል። ሐጂ በሺር ዳውድ እና ሸይኽ ዐብዱልከሪም ኑርሑሴን ተባባሪ ኤዲተሮች በመሆን መሥራታቸውን ሠነዶች ያመለክታሉ። የትርጉሙን ረቂቅ በማስተካከል የተሳተፉት ሸይኽ ቡሽረል ከሪም ሙስጠፋ፣ ሐጂ ዩሱፍ ዐብዱረሕማ ገራድ፣ ቃዲ ሙሐመድ ዐብዱረሕማን፣ ሐጂ አሕመድ ዳለቲ እና ሐጂ መንዛረሁ ከቢር ሑሴን ናቸው።