"ኡማ ቲቪ " Tv


Channel's geo and language: Iran, Persian
Category: not specified


መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+UAKV38o3WF-YJ6jh

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Iran, Persian
Category
not specified
Statistics
Posts filter


በሐማስ ስር ያለው የቀሳም ብርጌድ ሰራዊት አባላት የሆኑት ጁሙዓ ሳሊም እና ፈትሒ ሳሊም በዛሬው እለት በዌስት ባንክ ከወራሪው የእስራኤል ሰራዊት ጋር ሲፋለሙ ተሰውተዋል።
ብዙ ጊዜ አፍሪካዊያኑን አረንጓዴውን የወራሪ ሬንጀር ለብሰው ሲዋጉ እንጂ አላየንም ነበር።በነዚህ ሁለት ወጣቶች ለአቅሷ ደሙን የሰጠ አፍሪካዊም አግኝተናል።
አሏህ ይርሐማቸው

5k 0 12 23 274

ሂክማ ዩኒቨርሲቲ በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ እየተገነባ የሚገኝ እስላማዊ ዩኒቨርሲቲ ነው

ይህ ዩኒቨርሲቲ በዉስጡ የተለያዩ የትምህርት ዘርፎችን ይሰጣል
የሂክማ ዩንቨርስቲን ግንባታ የገቢ እንቅስቃሴ ለማጠናከር ከየእቅጣጫው እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል
ሰዑዲ አረቢያ ሪያድ ላይ እ.አ.አ ጃንዋሪ 9-01-2025 በዕለተ ሐሙስ ማንም የማይቀርበት ታላቅ ህዝባዊ ውይይት የገቢ ማሰባሰቢያ ለማድረግ ቀነ ቀጠሮ ተይዟል
ቀጣዩ ትውልድ በዕውቀት የታነጸ እና የተሻለ ደረጃ እንዲዲደርስ ሂክማ ዩኒቨርሲቲን ማጠናከር የኔ ፣ያንተ፣ያንቺ እና የሁላችንም ግዴታ ነው❗


በኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር አማካኝነት ከተለያዩ የሃገራችን አካባቢዎች ተፈናቅለው ወሎ ደሴ ገራዶ፣ ሀርቡ፣ ደጋንና አርጎባ ሰንቀሌ ለሚገኙ 2,300 ለሚሆኑ አቅመ ደካሞችና የሸሪዓ እውቀት ተማሪዎች የ4.7 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል።

© ኢብኑ መሱድ ኢስላሚክ ሴንተር


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
የአክሱም እህቶቻችን ሂጃብ ካላወለቃችሁ አትማሩም ተብለዋል።

ይኸው እንግዲህ እዚህ ደረጃ ደርሰናል።


"..እኛ የጠየቅነው የዩኒፎርማችንን ተመሳሳይ ሂጃብ ለብሰን ትምህርታችንን እንድንማር ነው። ነገር ግን ፀጉራቹሁ ካልታዬ መማር አትችሉም ተባልን"

- የአክሱም ከተማ ሙስሊም ተማሪዎች

በትግራይ ክልል የአክሱም ከተማ ሙስሊም ተማሪዎች በሂጃባቸው ምክንያት ትምህርት አቋርጠው ያለመፍትሔ መቀመጣቸውን ገልጸዋል።

"እኛ ከትምህርት ቤቶቹ ዩኒፎርም ጋር የሚመሳሰል ሀይማኖታችን በሚያዘው መሰረት ሂጃብ ለብሰን ትምህርታችንን እንማር ብለን ነው የጠየቅነው የሚሉት ተማሪዎቹ ነገር ግን ፀጉራቹሁ ካልታየ መማር አትችሉም ተብለን ከትምህርት ገበታ ተፈናቅለናል" ብለዋል።

የ12ኛ ክፍለ ዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ለመውሰድ ፎርም የሚሞላበት የመጨረሻ ቀን ነገ ረቡዕ እንደሆነ የገለፁት ተማሪዎች "ሂጃብ ካላወለቃችሁ" በመባሉ ምክንያት አንድም ሙስሊም ተማሪ ፎርሙን አለመሙላቱን ተናግረዋል።

የከተማዋ መጅሊስ በዛሬው ዕለት ከወረዳው የፀጥታ ሀላፊዎች እና ከክልሉ የፀጥታ ቢሮ ተወካዮች ጋር "በከተማዋ አድማ እንዲቀሰቀስ አድርጋችኋል" በሚል ስብሰባ መቀመጣቸውን የተናገሩ ሲሆን "ይህ አድማ አይደለም፣ ሀይማኖታዊ መብታቸውን ነው የጠየቁት" የሚል ምላሽ መስጠታቸውን ገልፀዋል።

ተማሪዎቹ ትምህርት አቋርጠው የሚቆዩበት ጊዜ እየረዘመ በመጣ ቁጥር በተማሪዎቹ ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ቀላል ባለመሆኑ የሚመለከተው አካል አስቸኳይ እልባት እንዲሰጥ ጠይቀዋል።


የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፡-
-" የሑሲ ጥቃቶችንና ኢራን ለእነሱ የምታደርገውን ድጋፍ አስመልክቶ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲያደርግ ለፀጥታው ምክር ቤት አቅርበናል።"
-"ሁሲዎች በእስራኤል ላይ ጥቃት ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።የመርከብ እና የመገበያያ ነፃነት ስጋት ላይ ናቸው።በአካባቢው እና በመላው አለም ላይ ስጋት ፈጥረዋል።"

የፀጥታው ምክር ቤት ከዚህ በፊት የእስራኤል መንግስት በጋዛ እየፈፀመች ያለውን ጥቃት እንድታቆም አዞ ነበር


ትናንት ማታ የጀመርነው የወንድማችንን እናት እናሳክም በሚል ስናደርግ የነበረው እንቅስቃሴ በአላህ ፍቃድ በእናንተ ሰበብ ለወንድማችን ለእናቱ ህክምና የሚያስፈልገው ገንዘብ ተሟልቶል አልሀምዱሊላህ ወደ አካውንቱ 65ሺ ብር ገብቷል ። የተሳተፍቹህ ሁሉ ተባረኩ አላህ ሀጃችሁን ያውጣው አላህ ይውደዳቹህ ።

ቀጣይ ሂደቱን እየተከታተልን የምንገልፅ ይሆናል ።


ማስታወቂያ

ዛሬ አንድ ለበርካቶች ጥያቄ መሰረት እንደ ፍላጎታቹህ ለ10 ቀናት እና ከዛ በላይ በኡምራ ፕሮግራም መቆየት ለምትፈልጉ እነሆ እንኳን ደስ አላቹህ ይላቹሀል ኢትዩ ቱር ትራቭል

🕋 ከጥር 8 በፈለጉት የፓኬጅ አይነት በመካና በመዲና የምቆዩበት ልዩ የኡምራ ፓኬጅ በኢትዩ ቱር ኤንድ ትራቭል ተዘጋጅቶል

በተመጣጣኝ ዋጋ እና በልዩ መስተንግዶ ልዩ የዒባዳ ግዜን ማሳለፍ ከፈለጉ የኛ ቤተሰብ ይሁኑ

🌟 ልዩ ጥቅል ከ ኢትዮ ቱር 🌟
ከጥር 8 ጀምሮ

ለ7 ቀን(3ቀን መካ 3 ቀን መዲና)
ለ 12 ቀን (8ቀን መካ 4ቀን መዲና)
ለ 15 ቀን (10 ቀን መካ 5ቀን መዲና)

🌟ምንሰጣቸው አገልግሎቶች🌟
✅ የኡምራ ቪዛ
✅ ቲኬት
✅ ሆቴል
✅ ትራንስፖርት
✅ ምግብ እና ላውንደሪ
✅ የሳኡዲ ሲም ካርድ

ለበለጠ መረጃ
+251946555777
+251946888777
8924(አጭር ኮድ)


"ሒጃብ ለብሳችሁ መማር አትችሉም" በሚል በአክሱም የሚኖሩ ሙስሊም ሴቶች ከፍተኛ እንግልት ውስጥ ናቸው። የክልሉ መጅሊስ የቻለውን ያክል ቢጥርም የሚሰማው እንዳጣ በደብዳቤ ገልጿል። እምነቱን ተንተርሶ የራስን ወገን የመጨቆን የከረመ በሽታ መቸ ይሆን የሚለቀን?ተማሪዎቹ ትምህርት ቤት እንዳይገቡ ከተከለከሉ 3 ሳምንት አልፏቸዋል፣ ለማትሪክ ፎርም እየተሞላ ቢሆንም ሙስሊም ተማሪዎች ግን መሙላት አልቻሉም።


ቅዱስ ቁርኣንን ወደ ቋንቋዋ ለመመለስ የተዘጋጀችው ሀገር

ቅዱስ ቁርኣን ከወረደበት የዐረቢኛ ቋንቋ፤ አማርኛን ጨምሮ ወደተለያዩ የዓለም ቋንቋዎች ተተርጉሞ ይገኛል። የቁርኣን የተመረጡ አንቀፆች እስካሁን ድረስ ወደ 114 ቋንቋዎች የተተረጎመ ሲሆን፣ ሙሉ ቃሉ የተመለሰው ደግሞ ወደ 47 ቋንቋዎች ነው።

በዚህ ሳምንት ደግሞ የሰሜን አፍሪካዋ ሀገር ሞሮኮ፣ በሀገሯ ወደሚነገር ቋንቋ የመተርጎም እቅድ መያዟን ይፋ አድርጋለች። የሀገሪቱ የእስልምና ጉዳዮች ሚኒስቴር እንዳሳወቀው ከሆነ፣ የቁርኣንን ሙሉ ቃል ወደ አማዚግ ቋንቋ ለመመለስ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።

አማዚግ የተሰኘው ቋንቋ እ.አ.አ ከ2011 አንስቶ የሞሮኮ ይፋዊ ቋንቋ በመሆን እያገለገለ ነው። ተማዚግት በሚል ተለዋጭ መጠሪያ የሚታወቀው ይህ ቋንቋ፣ ከአፍሮ ኤዥያቲክ ቋንቋ ቤተሰብ የሚመደብ ነው። ከ30 በመቶ በላይ በሚሆኑ ሞሮካዊያንም ይነገራል።

በኢትዮጵያ ወደ አማርኛ ቋንቋ የተተረጎመው ቅዱስ ቁርኣን ለኅትመት የበቃው በ1961 ነው። ትርጉሙ የተሠራው በሐጂ ሙሐመድ ሣኒ ሐቢብ እና ሸይኽ ሰይድ ሙሐመድ ሳዲቅ መሆኑ ይታወቃል። ሐጂ በሺር ዳውድ እና ሸይኽ ዐብዱልከሪም ኑርሑሴን ተባባሪ ኤዲተሮች በመሆን መሥራታቸውን ሠነዶች ያመለክታሉ። የትርጉሙን ረቂቅ በማስተካከል የተሳተፉት ሸይኽ ቡሽረል ከሪም ሙስጠፋ፣ ሐጂ ዩሱፍ ዐብዱረሕማ ገራድ፣ ቃዲ ሙሐመድ ዐብዱረሕማን፣ ሐጂ አሕመድ ዳለቲ እና ሐጂ መንዛረሁ ከቢር ሑሴን ናቸው።


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
🔍የት ነው ትምህርቱ❓
ከቤቶ ሆነው በኦንላይን

🔍ለምን ያህል ጊዜ ነው❓
ትምህርቱ ለ3 ወር የሚሰጥ ይሆናል

🔍በሳምንት ስንት ቀን ነው❓
1 ቋንቋ በሳምንት 3 ቀን እናስተምራለን

🔍ሰዓቱስ❓
ማታ ከ3-4 ሰዓት (በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር)

🔍ለጀማሪ ብቻ ነው❓
አይደለም! ለጀማሪም ለመሀከለኛም ለላቀ ደረጃም የተለያዩ ክፍሎች ይኖራሉ

🔍ብቻዬን ነው ምማረው❓
አይደለም አንድ የኦንላይን ክፍል 15 ተማሪዎች ይኖሩታል

🔍ከጓደኞቼ ጋር አንድ አይነት ክፍል ተመዝግበን መማር እንችላለን❓
ከጓደኛም ከቤተሰብም ጋር በጋራ መመዝገብ ይችላሉ

🔍አንድ ቋንቋ ብቻ ነው መማር ምችለው❓
በተለያየ ፈረቃ ሚገኙ ሁለት ቋንቋዎች መማር ይችላሉ

🔍ክፍያው ስንት ነው ታድያ❓
በወር 1000 ብር ሲሆን ለ3 ወር ትምህርት 3000 ብር ይሆናል

🔍ሁለት ቋንቋ ከተማርኩኝ ቅናሽ አታረጉልኝም❓
ሁለት ቋንቋ ለሚማሩ ከፍተኛ ቅናሽ አለን

🔍ምዝገባ እስከመቼ ነው❓
ምዝገባ ከህዳር 17 እስከ ታህሳስ 25 ይቆያል


አሁኑኑ ይመዝገቡ! 🖥
ለበለጠ መረጃ በዚህ አድራሻ ይፃፉልን
➡️https://t.me/brightmanagement
ወይም
በነዚህ ቁጥሮች ይደውሉልን
➡️ 0925659999
➡️ 0911278182


ለተጨማሪ መረጃዎች ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/brightlanguagescenter
https://t.me/Brighttutorialcenter


ብራይት የቋንቋ ማዕከል
#Brightlanguagescenter


ስለ አክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሒጃብ ክልከላ ተጨማሪ መረጃ

📍በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን አክሱም ከተማ በአክሱም አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምሀርት ቤት ሙስሊም ተማሪዎች "ሂጃባችሁን ካላወለቃችሁ አትማሩም" በሚል ከትምህርት ገበታ ከተፈናቀሉ ከሶስት ሳምንት በላይ እንደሆናቸው ተማሪዎቹ ገልፀዋል

📍ተማሪዎቹ ሂጃባችሁ ካላወለቃችሁ የ12ኛ ክፍል ፎርም መሙላት አትችሉም ተብለዋል።

📍በዚህም ምክንያት በርካታ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸው ተገልጿል።

📍ጉዳዩን በተመለከተ #የአክሱም_የወረዳ_መጅሊስ ከከተማ እስከ ክልል ላሉ የትምህርት ቢሮዎች እና የፀጥታ ቢሮዎች ጉዳዩን ማመልከታቸውን ገልፀው ይሁንና እስካሁን መፍትሔ አላገኘንም ብለዋል። ደብዳቤው መመልከት ትችላላችሁ።

📍#የትግራይ_ክልል_እስልምና_ጉዳዮች_ከፍተኛ_ምክር_ቤት በበኩሉ ችግሩን በተመለከተ መፍትሔ ለማምጣት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሰራን ነው ያለ ቢሆንም እስካሁን ግን ምንም አዲስ ነገር እንደሌለ ተማሪዎቹ ገልጸዋል።

📍በከተማዋ የዘንድሮ 12ኛ ክፍል ዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ፎርም እየተሞላ ቢሆንም ሙስሊም ተማሪዎች ግን ሂጃብ ካላወለቃችሁ በሚል ፎርም እንዳይሞሉ መደረጋቸውን ገልፀዋል። መፍትሔ አጥተን ቤታችን ተቀምጠናል የሚሉት ተማሪዎቹ የሚመለከተው አካል እልባት እንዲሰጣቸው ተማፅነዋል።


አዲስ መፅሐፍ በገበያ ላይ...

ገንዘብና ወለድ - እውነታ እና ብዥታ

በሸይኽ ኢልያስ አህመድ የተዘጋጀ በአይነቱ ልዩ ጥናታዊና ወቅታዊ መፅሐፍ

ዋጋ = 400 ብር

በሚከተሉት መደብሮች ይገኛል
1) ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር (18 ማዞርያ)
2) አት'ተውባ የመጻሕፍት መደብር (አንዋር መስጂድ)
3) አት'ተቅዋ የመጻሕፍት መደብር (ቤተል)
4) ዛዱል መዓድ የመጻሕፍት መደብር (ፋሪ)

الحمد لله الذي بنعمته تتم الصالحات!

መረጃው እንዲዳረስ ሼር አርጉ
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+UAKV38o3WF-YJ6jh


በሶሪያ በተለያየ ስያሜ ይገኙ የነበሩ ታጣቂ ኃይላት በአንድ ወጥ የመከላከያ ሚንስትር ስር ተጠቃለው ለመስራት ከስምምነት ደርሰዋል።
ለተጨማሪ መረጃ ለማገኘት
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+UAKV38o3WF-YJ6jh

5.4k 0 2 14 149

«ወደ ት/ቤት የመጡ ሴት ልጆቻችንን እንጠንቀቅላቸው ::

Home and school should work together.
ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን የሚያስተምሩት ከወላጅ ጋር በመተባበር ነው :: ወላጅ እና ት/ቤት አብረው ልጆችን የሚያስትምሩ partners ናቸው :: ት/ቤት የቤት extention ነው :: አላማውም አንድ ነው ::  ልጅችን አስተምሮ ለቁምነገር ማብቃት ነው ::

Consistent message between home and school is vital for student training.
ሂጃብ ት /ቤት ውስጥ መልበስ  የቤተሰብ ምርጫም, መብትም, life style, እምነትም ነው:: መከበርም አለበት :: የትምህርት ቤት የደንብ ልብስ የቀለም ምርጫ እኩዋን ቢኖር የሂጃብ ከለር ላይ መስማማት ይቻላል :: ትምህርት ቤት የሳይንስ እና የምረምር ቦታ እንደመሆኑ ሂጃብ መልበስ እና አለመልበስ ከዋናው የትምህርት አላማ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም ::

ሀገራችን ት/ቤቶችን መምራት ላይ ስልጠና እና ግንዛቤ ማሳደግ አለባት ::  ወደ  ትምህርት ስርአታችን ስንመጣ ብዙ አሳሳቢ እና አንገብጋቢ ጉዳዮች አሉ ::

የተማሪዎች ምግብ, ሳይንስን የምናስተርበት መንገድ, ተማሪዎችን የሕይወት ዘመን ተማሪዎች እንዲሆኑ ማሰልጠን, ተሰጦ እና ዝንባሌአቸውን ተርድቶ በዛ መስመር እንዲያድጉ ማገዝ..... የመሳሰሉት በርካታ ጉዳዮች አሉ ::እነሱ ላይ ብንሰራ ልጆቹን ይጠቅማል ::

በራሳችን ላይ እንዲሆን የማንፈልገውን ነገር በሌሎች ላይ አንፍቀድ ::  ለመማር የመጡ ሴት ልጆችን በሰበቡ አትገቡም ማለት አላማው ግልፅ አይደለም እና መታረም አለበት ::

ትምህርት የአእምሮ ሥራ ነው :: ህንድን ከቅኝ ግዛት ነፃ ያወጣው ዝነኛው መሀትማ ጋንዲ በሂንዱ ባህል ቤት ወስጥ የተሰራ ልብስ አገልድሞ ነው አለም አቀፍ በጎ ተፅእኖ ማሳረፍ የቻለው ::  ጋንዲ ያንን እርምጃ በመውሰዱ መላው ህንድ የባህል ልብስ አብዮት አስንስቶ አሁን ህንድ ውስጥ የጨርቃጨርቅ ሚንስቴር አለ :: ህንድም ለዓለም የልብስ ኤክስፖርተር  ሆነች :: መንሻው ግን የጋንዲ የባህል ልብስ ለመልበስ መወሰኑ ነበር:: 

ትምህርት ቤቶች አላማቸው መሆን ያለበት ሰዎች ራሳቸውን እንዲያገኙ እና ውስጣቸው ያለውን እምቅ አቅም ለማውጣት  ማገዝ ነው ::

ባንዳንድ የሀገራችን ክፍል ሂጃብ አትለበሱም በማለት ብዙ ችግር ተቋቁመው ት /ቤት የመጡ ሴት ልጆቻችንን ከበር ማስመለስ አላማው ግልፅ ስላልሆነ የሚመልከታችሁ አካላት መፍትሄ እንዲሰጡ እና
የ school management ስልጠናም በሰፊው እንዲሰጥ አደራ እላለሁ ::

#ministryofeducation
Ministry of Health,Ethiopia
Office of the President, Ethiopia
Office of the First Lady-Ethiopia
Office of the Prime Minister-Ethiopia

#UNICEF »


©: ፍሬአለም ሺባባው


የቱርኩ ፕሬዝዳንት :-
-"እየጨመረ የመጣው የእስራኤል ጥቃት በሶሪያ ያለውን አብዮት ለማጨለምና የህዝቦቿን ተስፋ ለማጨናገፍ ያለመ ነው።"

-"ይዋል ይደር እንጂ እስራኤል ሁኔታውን ተጠቅማ በሶሪያ ከያዘችበት ምድር ትወጣለች።"

አልጀዚራ


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ፈረንሳይ በቻድ የሚገኙ ሰራዊቷን ማስወጣት ጀመራለች!
የቻድ መንግስት ከሳምንት በፊት ከፈረንሳይ ጋር ያለወን ወታደራዊ ትብብር እንደሚያቋርጥ ገልፆ ነበር።


በአፋር ክልል የሚገኘው የአዋሽ አካባቢ፤ ባለፈው መስከረም እና ጥቅምት ብቻ 10 የመሬት መንቀጥቀጦችን አስተናግዷል። በአካባቢው እስካሁን የተመዘገበው ከፍተኛ የርዕደ መሬት መጠን፤ በሬክተር ስኬል 4.9 የተለካ መሆኑም ተገልጿል።

ከመተሐራ ከተማ አቅራቢያ 13 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ቦታ ትላንት ሰኞ ምሽት የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ መስሪያ ቤት  ያስታወቀ ሲሆን ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የተሰማው የትላንት ምሽት ርዕደ መሬት፤ በሬክተር ስኬል 4.9 የተመዘገበ መሆኑን መስሪያ ቤቱ ገልጿል።

የትላንት ምሽቱ የመሬት መንቀጥቀጥ ሃያ አራት ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በአካባቢው ለሁለተኛ ጊዜ የተከሰተ ነው። ትላንት ለሊት 10 ሰዓት ከ13 ደቂቃ አካባቢ፤ ከአዋሽ ከተማ አምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባለ ስፍራ ተመሳሳይ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደነበር በመላው ዓለም የደረሱ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶችን የሚመዘግቡ ተቋማት ያወጧቸው መረጃዎች አመልክተው ነበር።

የትላንት ለሊቱን የመሬት መንቀጥቀጥ የመዘገቡ እነዚሁ ተቋማት፤ መጠኑ መጠነኛ የሚባል እና በሬክተር ስኬል 4.6 የሚለካ እንደሆነ ይፋ አድርገዋል። ትላንት ሰኞ ታህሳስ 14፤ 2017 ምሽት 4 ሰዓት ከ40 ገደማ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ፤ ባለፈው መስከረም ወር መጨረሻ በአዋሽ አካባቢ ከተመዘገበው ርዕደ መሬት ጋር በመጠን እኩል መሆኑም ተገልጿል።

ክስተቱ በቀጣይ በሰው እና ንብረት ላይ ጉዳት እንዳያስከትልም የሚመለከታቸው የፌደራልና የክልል አካላት በጉዳዩ ላይ በትኩረት እንዲሰሩ ጥሪ ቀርቧል።


ተደራራቢ በደል በአክሱም ሙስሊሞች!

የአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ ለብሳችሁ መማር አትችሉም ተብለው ይኸው በር ተዘግቶባቸው ቆመው የሰሚ ያለህ እያሉ ይጣራሉ! በአክሱም ሙስሊሞች ላይ የሚደርስ በደል በዛ! ተደራራቢ ጭቆና! መስጊድ፣ የቀብር ቦታ እና የመማር መብት ተነፍገዋል! ለአክሱም ሙስሊሞች ድምፅ እንሁን!#Justice_for_Axum_muslims

19 last posts shown.