በአፋር ክልል የሚገኘው የአዋሽ አካባቢ፤ ባለፈው መስከረም እና ጥቅምት ብቻ 10 የመሬት መንቀጥቀጦችን አስተናግዷል። በአካባቢው እስካሁን የተመዘገበው ከፍተኛ የርዕደ መሬት መጠን፤ በሬክተር ስኬል 4.9 የተለካ መሆኑም ተገልጿል።
ከመተሐራ ከተማ አቅራቢያ 13 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ቦታ ትላንት ሰኞ ምሽት የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ መስሪያ ቤት ያስታወቀ ሲሆን ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የተሰማው የትላንት ምሽት ርዕደ መሬት፤ በሬክተር ስኬል 4.9 የተመዘገበ መሆኑን መስሪያ ቤቱ ገልጿል።
የትላንት ምሽቱ የመሬት መንቀጥቀጥ ሃያ አራት ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በአካባቢው ለሁለተኛ ጊዜ የተከሰተ ነው። ትላንት ለሊት 10 ሰዓት ከ13 ደቂቃ አካባቢ፤ ከአዋሽ ከተማ አምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባለ ስፍራ ተመሳሳይ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደነበር በመላው ዓለም የደረሱ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶችን የሚመዘግቡ ተቋማት ያወጧቸው መረጃዎች አመልክተው ነበር።
የትላንት ለሊቱን የመሬት መንቀጥቀጥ የመዘገቡ እነዚሁ ተቋማት፤ መጠኑ መጠነኛ የሚባል እና በሬክተር ስኬል 4.6 የሚለካ እንደሆነ ይፋ አድርገዋል። ትላንት ሰኞ ታህሳስ 14፤ 2017 ምሽት 4 ሰዓት ከ40 ገደማ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ፤ ባለፈው መስከረም ወር መጨረሻ በአዋሽ አካባቢ ከተመዘገበው ርዕደ መሬት ጋር በመጠን እኩል መሆኑም ተገልጿል።
ክስተቱ በቀጣይ በሰው እና ንብረት ላይ ጉዳት እንዳያስከትልም የሚመለከታቸው የፌደራልና የክልል አካላት በጉዳዩ ላይ በትኩረት እንዲሰሩ ጥሪ ቀርቧል።