ኢትዮጵያን ሊለውጥ ይችላል ብለው የሚያምኑበትን ሃሰብ ለመቀበል ቅድመ ሁኔታ አያስቀምጡም፡፡ መምህርነት እና ፖለቲከኛነት አልተጋጨባቸውም፡፡ ትምህርት ቤት ሲሆኑ ምርጥ አስተማሪ እና ተመራማሪ፣ በፖለቲካው መድረክም የሃሳብ ተሟጋች ናቸው፡፡ ፖለቲካንም ሆነ አስተማሪነት ሳይቀላቅሉ በየራሳቸው መድረክ አሳምረው ይወጡአቸዋል፡፡
ከሦስት አሥርተ ዓመታት በተሻገረው የአደባባይ የፖለቲካ እንቅስቃሴያቸው ብዙ ችግሮችን በግጭት እና በጠመንጃ አፈሙዝ መፍታት መሞከር ልማድ በሆነባት ኢትዮጵያ ሁሉንም አሸናፊ የሚያደረገው በጠመንጃ መሸናነፍ ሳይሆን የሃሳብ ሜዳ የተሻለ መሆኑን በተግባር አስመስክረዋል፡፡
በኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት ሰለማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ በማድረግ የሚታወቁት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲም በመምህርነት እንዲሁም በትምህርት ሚኒስትር ዴዔታነት ሀገራቸውን አገልግለዋል፡፡
ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ጳጉሜን 4 ቀን 2012 ዓ.ም የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሹመው ሲያገለግሉ መቆየታቸው የሚታወስ ሲሆን በዛሬው ዕለት ባደረባቸው ህመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
#EBC
@ZIONRESEARCH