የተውሒድ ትምህርቶች
ክፍል ስድስት
የተውሒድ ትሩፋቶች (የቀጠለ)
7. እንደዚሁም ተውሒድ በዱንያም በአኼራም የስኬትና መዳን ሰበብ ነው። አላህ ሱ.ወ. እንዳለው
قَدۡ أَفۡلَحَ مَن تَزَكَّىٰ
“የተጥራራ ሰው በእርግጥ ዳነ።”
ማለትም ራሱ ከሽርክ ወንጀል የተጥራራ ሰው ማለት ነው። ራሱን ከጉድለትና ከዝቅተኛ ስራዎች ንፁህ ያረገና ነገር ግን ከሽርክ ራሱን ንፁህ ካላደረገ የተጥራራ ሰው አይሆንም። ሽርክ ነጃሳ ሲሆን ተውሒድ ደግሞ ጠሀራ ነው። አዎ ተውሒድ ንፁህ ነው፤ ሽርክ ደግሞ ነጃሳ። የተጥራራ ሰው በእርግጥ ዳነ። በዚህም ምክንያት ረሱል صلى الله عليه وسلم ገበያ ውስጥ በሰዎች መካከል እየተዘዋወሩ “እናንተ ሰዎች ሆይ ላኢላሀ ኢለላህ በሉ ትድናላችሁ” ይሉ ነበር። ስለዚህ መዳን ለተውሒድ ባለቤቶች እንጂ ለሌላ አይደለም። መዳን (ፈላሕ) የዱንያና የአኼራ መልካም ነገሮችን በሙሉ ጠቅልሎ የያዘ ነው። ትልቁ ደረጃውም በጀነት መደሰትና ከእሳት ነፃ መውጣት ነው። በዚህም ምክንያት ከቃላቶች ውስጥ ከሁሉም በላይ መልካም ነገሮችን ጠቅልሎ የያዘ ቃል ‘ፈላሕ’ (መዳን እና ስኬት) የሚለው ቃል ነው። አንድ የአላህ ባሪያ የዱንያና የአኼራ መልካም ነገሮችን ጠቅልሎ ሊይዝ አይችልም በተውሒድ ቢሆን እንጂ። ይህች ኡመት በተውሒድ እንጂ በጉዳዮቿ ላይ ስኬትን ፈፅሞ አታገኝም። ይህች ኡመት ከተውሒድና በሰዎች ሁለንተናዊ ኑሮ ላይ ተውሒድን ከማረጋገጥ በራቀች ጊዜ ጥመት የከበባት፤ ጃሂሊያ የተንሰራፋው፤ ሽርክም የተስፋፋው ለዚህ ነው። ስለዚህም በተውሒድ እንጂ ከዚህ አዘቅት መውጣት አንችልም። በተውሒድ እንጂ ስኬትና መዳን የለም።
8. በተጨማሪም በግለሰብም ይሁን በማህበረሰብ ደረጃ ተውሒድ ከሚያስገኛቸው በረከቶች ውስጥ አላህ ተውሒድን ለእርዳታና ድል ሰበብ ማድረጉ ነው። አላህ ይላል
لَّا تَجۡعَلۡ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ فَتَقۡعُدَ مَذۡمُومٗا مَّخۡذُولٗا
ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ አታድርግ የተወቀስክ ረዳት የሌለህ ትኾናለህና፤
ለሙሽሪክ ሰው ረዳት-የለሽነትን አላህ ወስኖበታል። ሙሽሪክ ረዳት የለሽ ነው። በዱንያውም ሆነ በአኼራው ስኬትንና መዳንን አያገኝም፤ አላህም አይረዳውም። እንደዚሁም አላህ ዘንድና አውሊያኦቹ ዘንድም ወራዳ ነው። ሽርክ መርጋት እንደሌላት መጥፎ ዛፍ ነው። በሷ መዳን አይቻልም። ለዚህም ነው ሙሽሪክ እርዳታ አያገኝም፤ ጠማማና ግራ የተጋባ ሆኖ ይቀራል። ሙሽሪክ በሽርኩ ምክንያት ረዳት የለሽ ከሆነ ሙወሒድ ደግሞ በተውሒዱ ሰበብ እርዳታና ድልን የሚያገኝ ነው። በዚህም ምክንያት አላህን አንድ አድርጎ የተገዛና ሀይማኖቱን ለአላህ ያጠራና በሱ ላይ ብቻ የተንጠለጠለ ሰው እሱ በሁሉምቢሆን ሁኔታዎቹ ውስጥ ምስጉንና እርዳታ የሚያገኝ ይሆናል። ይህች ኡመታችን ይህ የአላህ ኒዕማ በጣም ያስፈልጋታል። እርዳታና ድል ማድረግ በተውሒድ እንጂ በጠላቶቻችን ላይ እግገዛን አናገኝም፤ ድልም አይሰጠንም በተውሒድ እንጂ።
9. የአላህ ባሮች ሆይ አደራችሁን ፅናት እናድርግ! አላህ ተውሒድን ትልቁ የፅናት ሰበብ አድርጎታል። ይህም ከተውሒድ በረከቶች ውስጥ አንዱ ነው። ተውሒድ ዲን ላይ ለመፅናት ትልቁ ሰበብ ነው። አላህ ሱ.ወ. አለ
يُثَبِّتُ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ بِٱلۡقَوۡلِ ٱلثَّابِتِ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا وَفِي ٱلۡأٓخِرَةِۖ
አላህ እነዚያን ያመኑትን በቅርቢቱም ሕይወት በመጨረሻይቱም (በመቃብር) በተረጋገጠው ቃል ላይ ያረጋቸዋል።(ያፀናቸዋል)
አላህ ለነዚያ ላመኑት የተውሒድ ባለቤቶች ፅናትን ወስኖላቸዋል። አላህ የተውሒድን ንግግርንም ‘የተረጋገጠው (ፅኑ) ቃል’ ብሎ ሰይሞታል። እንደዚሁም ተውሒድንም በቴምር ዛፍ መስሎታል። የቴምር ዛፍ ከዛፎች ሁሉ የበለጠ ፅኑና የረጋ ነው።
أَلَمۡ تَرَ كَيۡفَ ضَرَبَ ٱللَّهُ مَثَلٗا كَلِمَةٗ طَيِّبَةٗ كَشَجَرَةٖ طَيِّبَةٍ أَصۡلُهَا ثَابِتٞ وَفَرۡعُهَا فِي ٱلسَّمَآءِ
አላህ መልካምን ቃል ሥርዋ (በምድር ውስጥ) የተደላደለች ቅርንጫፍዋም ወደ ሰማይ (የረዘመች) እንደሆነች መልካም ዛፍ አድርጎ ምሳሌን እንዴት እንደገለጸ አላየኽምን
መልካም ቃል የተባለው የተውሒድ ንግግር ወይም ‘ላኢላሀ ኢለላህ’ የምትለዋ ቃል ናት። ስለዚህ በአላህ ዲን (ሀይማኖት) ላይ መፅናት የፈለገ ሰው ተውሒዱን ለአላህ ያጥራ፤ እሱ ጠንካራው ገመድ ነውና።
فَمَن يَكۡفُرۡ بِٱلطَّـٰغُوتِ وَيُؤۡمِنۢ بِٱللَّهِ فَقَدِ ٱسۡتَمۡسَكَ بِٱلۡعُرۡوَةِ ٱلۡوُثۡقَىٰ لَا ٱنفِصَامَ لَهَاۗ وَٱللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ
በጣዖትም የሚክድና በአላህ የሚያምን ሰው ለርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ። አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው።
10. ተውሒድ ችግርን ለመከላከልና ከሀዘን ለመውጣት ትልቁ ሰበብ ነው። አዎ! አንተ ሀዘንና ሀሳብ ያስጨነቀህ ሰው ሆይ! አንተ ችግርና ሀዘን የበዛብህና የዱንያ ችግር የተደራረብህ ሰው ሆይ! አንተ የተውሒድ ባለቤት ሆይ! ችግሮችን ለመከላከልና ከነዚህ ሀዘኖች ነፃ ለመውጣት ትልቁ ሰበብ በልባችን እያለ ተስፋ መቁረጥና ማዘን ለምንድን ነው? የነብዩን صلى الله عليه وسلم ፈለግ የተከታተለ ሰው ችግር ባጋጠማቸውና ሀዘንና ሀሳብ በደረሰባቸው ጊዜ አላህን የሚለምኑት እንዴት ነበር? በምን ነበር ወደ አላህ የሚቃረቡት? በምን ነበር አላህን የሚለምኑት? ቡኻሪና ሙስሊም በሰሒህ ሐዲሶቻቸው በዘገቡት የኢብን ዓባስ ሐዲስ ረሱሉላህصلى الله عليه وسلم ሀዘን በደረሰባቸው ጊዜ
لا إله إلَّا اللَّه العظيمُ الحليمُ, لا إله إلَّا اللَّه ربُّ العرشِ العظيمِ, لا إله إلَّا اللَّه ربُّ السماواتِ وربُّ الأرضِ وربُّ العرشِ الكريمِ
”ትልቁና ቻዩ (ታጋሹ) ከሆነው አላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ የታላቁ ዓርሽ ጌታ ከሆነው አላህ ሌላ በእውነት የሚመለክ የለም፤ የሰማያት ጌታ፣ የምድር ጌታ፣ የተከበረው ዓርሽ ጌታ ከሆነው አላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም።“ ይሉ ነበር ብሏል::
ጠበሪይ እንዳለው ሰለፎች ይህንን ዱዓእ ‘ዱዓአል ከርብ’ (የጭንቅ ጊዜ ዱዓእ) ይሉት ነበር ብሏል። የሀዘን ጊዜ ዱዓን ተመልከት! እንዳለ በሙሉ ተውሒድ ነው። በመጀመሪያ ወደ አእምሯችን ቶሎ የሚመጣው ነብዩ صلى الله عليه وسلم ጉዳያቸውን፣ ሀዘናቸውንና ጭንቃቸውን ማንሳት እንደሚያበዙ ከመሆኑ ጋር ነብዩ صلى الله عليه وسلم ግን በሀዘን ጊዜ ዱዐቸው ተውሒድን እንጂ አያነሱም፤ በተውሒድ እንጂ ወደ አላህ አይቃረቡም። ”ትልቁና ቻዩ (ታጋሹ) ከሆነው አላህ በ ስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ የታላቁ ዓርሽ ጌታ ከሆነው አላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ የሰማያት ጌታ፣ የምድር ጌታ፣ የተከበረው ዓርሽ ጌታ ከሆነው አላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም።“
وقد جاء في مسند عبد ابن حميد مرفوعا: (كلمات الفرج لا إله إلَّا الله العظيم الحليم)