ደይፍ ይሉታል እንግዳ እንደማለት ነው። በእርግጥም እርሱ በወራሪዋ ደህንነቶች ታድኖ ሊገደል፣ ተጠፍሮም ሊያዝ ያልቻለ አሳዳጆቹ እጅ ሳይገባ ሀያ ዘጠኝ አመታቶችን ያስቆጠረ ሁሌም እንግዳ ሰው ነበር።
በማለዳ ተነስተው ከስክስ ጫማቸውን አጥልቀው ሮጠው ያላገኙት፣ ቴክኖሎጂ ተጠቅመው ያልደረሱበት የጥይት አሩር እየተኮሱ ቦንብ ከአውሮፕላን ቢያዘንቡ ፍፁም ሊገሉት ያልቻሉት የፍልስጤማዊያን ቁልፍ ሰው።
ለበይኪ ያ አቅሳ ብሎ በለጋ ዕድሜው የተነሳ ወጣትነቱን በትግል ያሳለፈ ትንታግ። ወንድሞቹ ሲሞሻለቁ፣ እህቶቹ በድምፅ አልባ መሳሪያ ሲወቁ ትከሻም ልቡም ለመሸከም አልፈቀዱለትም፡፡ ድንቡሽቡሽ ፊት ያላቸው እንቦቃቅላ ልጆቹን ትቶ፣ የእናቱን የእጅ ደበሳ ርቆ በጂሃድ ሜዳ ላይ ተሰየመ፡፡
የብሩህ አዕምሮ ባለቤት የመሐፈዝ አቅሙ ከፍተኛ የሰማውን ቀብ፣ ያየውን ልቅም አድርጎ የሚይዝ ፈጣን ነው። በየትኛውም ቴሌቪዥን ታይቶ አይታወቅም። ምንም አይነት ቴክኖሎጂ የማይጠቀም ባለ ዊልቸሩ የጦር መሪ።
አባቱ ልብስ እየሰፉ በአነስተኛ የዶሮ እርባታ እንቁላል እየሸጡ ያሳደጉት ልጅ ዛሬ ስሙን እንጂ ማንነቱን ለማወቅ የከበደው ሰው ሙሐመድ ደይፍ ነፍሱ ከምትወደው አላህ ጋር መገናኘቱን አቡ ዑበይዳ ተናግሯል። ሸሂድ ሆኗል ሲል እንባ እየተናነቀው አውስቷል። ኢላ ረህመቲላህ ያ አቡ ኻሊድ
©Mahi Mahisho