#መርጌታ_አምደ_ብርሃን_የባህል_ህክምና
#መዝሙረ_ዳዊት_በውስጡ_ያዛቸው_ጥበቦች ።
ከመዝሙረ ዳዊት ህእቡ ስሞች ጋር በማወዳጀት የሚጸለይ ጥበብ እንዳለ ሁኖ ትንሽ ስለ መዝሙረ ዳዊት ግንዛቤ ይፈጥርልን ዘንዳ ነው ይህንን ማቅረቤ!🌿
👉ይነበብ👇
❤️የመዝሙረ ዳዊት ዓይነቶች እንዴት መለየት እንችላለን? መዝሙራት በምን ዓይነት ሁኔታ ይከፈላሉ? አመዳደባቸውስ እንዴት ነው?❤️
👉የመዝሙራት ዓይነቶች መለየት አስቸጋሪ ቢሆንም ቀጥሎ የተጻፈው መረጃ ሊመራን ይችላል፡፡
የምስጋና መዝሙሮች ፦
👉ሀ) የእግዚአብሔርን ስም የሚያመስግኑ(መዝ 8፤ 20፤30፤34፤65፤68፤75፤76፤83፤87፤88፤91፤95፤107፤136)፡፡
ለ) ከመከራ ማዳኑን የሚያወድሱ (መዝ 18፤30፤34፤65፤75፤115፤116፤118፤138)፡፡
እነዚህ መዝሙሮች ዋና ትኩረታቸው እግዚአብሔርን ማመስገንና ማወደስ ነው፡፡ የሚያመሰግኑትም እግዚአብሔር ለፍጥረት ሁሉ ስላደረገውና እያደረገው ስላለው ድንቅ ሥራ ነው፡፡
👉ኃጢአተኛ በኃጢአቱ የሚያዝንበት(መዝ 6፤ 32፤38፤51፤102፤130፤143)፡፡
የዚህኛው ክፍል ዋና ትኩረት የኃጢአተኛ ሰው መጸጸትና ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርበው ልመና ነው፡፡ ኃጢአተኛው እግዚአብሔርን እንዳሳዘነ አምኖ በመገንዘብ ስሕተቱን ይቀበላል፤ ያዝናል፤ ይጸጸታል፤ ወደ እግዚአብሔር እየጸለየ ምሕረት ይለምናል፡፡
በመከራ ያለ ሰው የሚጸልይበት (የሚጽናናበት)(መዝ 3፤5፤7፤17፤20፤30፤31፤54፤59፤142)፡፡
በመከራ ውስጥ ያለ ሰው ስለደረሰበት መከራ ወደ እግዚአብሔር ይጮኻል፤ ይመጸናል፤ መከራውን ለእግዚአብሔር ይናገራል፤ መከራ እንዲደርስበት ያደረጉት ሰዎችን ይራገማል፤ በመከራ ውስጥ እያለ እግዚአብሔር ለምን ዝም እንዳለው ይጠይቃል፤ ከመከራው እንዲያወጣውም ይማጸናል፡፡
👉ዘማሪው እግዚአብሔርን ፣ ሕጉንና ቤቱን የሚናፍቅበት(መዝ 16፤ 17፤ 19፤ 40፤ 42፤ 45፤ 63፤ 73፤ 84፤ 119፤ 122፤ 128፤ 132)፡፡
እነዚህ መዝሙሮች የሚያተኩሩት በእግዚአብሔር ሕግ ፣ በቤተ መቅደስና በኢየሩሳሌም ከተማ ዙሪያ ላይ ነው፡፡ ቤተ መቅደስ እንደ የእግዚአብሔር ማደሪያ ቦታ የተጠቀሰበትም አለ፡፡ ስለዚህ ዘማሪው ወደ እግዚአብሔር ቤት ለመሄድ እንደሚናፍቅና እንደሚደሰት ይናገራል፡፡ ዘማሪው እግዚአብሔርን ለማየት እንደሚናፍቅ በተለያየ መልኩ ይገልጻል፤ ለምሳሌ ዋለያ የምንጭ ውሃ ለማግኘት እንደሚናፍቅ እኔም አንተን ለማየት እናፍቃለሁ ይላል(መዝ 42፡ 1)፡፡ እንዲሁም እግዚአብሔር ሆይ ! አንተ አምላኬ ነህ፤ አንተን ለማግኘት በብርቱ እናፍቃለሁ፤ ሁለንተናዬ አንተን ይመኛል፤ ውሃ በማጣት ደርቆ እንደተሰነጣጠቀ መሬት ነፍሴ አንተን ተጠማች ይላል(መዝ 63፡ 1)፡፡ በተመሳሳይ መልኩ የእግዚአብሔር ሕግ እንደ ብርሃን ሆኖ ሰዎች የሚመራ ስለሆነ መከበር እንዳለበትና የሚያከብሩትም በረከት እንደሚቀዳጁ የሚናገር ክፍል ነው፡፡ ለምሳሌ መዝሙር 128 ላይ እግዚአብሔር የሚያከብሩና ትእዛዛቱን በመጠበቅ የሚኖሩ ደስ ይበላቸው እያለ ይዘምራል(መዝ 128፡ 1)፡፡ በተጨማሪም ቃልህ እንደ መብራት ይመራኛል፤ ለመንገዴም ብርሃን ነው እያለ የእግዚአብሔር ሕግ ወደ እውነተኛው መንገድ እንደሚመራ ይናገራል(መዝ 119፡ 105)፡፡
ስለ መሲሕ የሚናገሩ(መዝ 2፤ 8፤ 16፤ 22፤ 40፤ 45፤ 69፤ 72፤ 110)፡፡
ይህ የሚያተኩረው እግዚአብሔር ስለሚልከው መሢሕና ስለዘሚያደርግለት ጥበቃና እንክብካቤ ላይ የሚናገር ነው፡፡ ይህ መሢሕ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ(መዝ 2፡ 7) ፣ በቀኙ እንደሚያስቀምጠውና(መዝ 110፡ 1) እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ካህን እንደሆነ ይናገራል(መዝ 110፡ 4)፡፡
ለትምህርት የሚሆኑ (መዝ 37፤ 49፤ 50፤ 52-55፤ 60፤ 74፤ 78፤ 89፤ 104፤ 119፤ 127)፡፡
እነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ብዙ ምክር አዘል አባባሎችና ትምህርቶች ተካተዋል፤ እነዚህም አባባሎችና ምክሮች መጽሐፈ ምሳሌ ውስጥ ከተገለጹት ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ናቸው፡፡ የሰዎች ትዕግሥት ፣ ታማኝነት ፣ ትሕትና ፣ በጎ ተግባራትና የመሳሰሉት ባሕርያት ወይም ክንውኖች ለሰው ልጅ መንፈሳዊ እርካታ እንደሚያሰጡና ከእግዚአብሔር ዘንድ ጸጋ እንደሚያቀደጁ ይናገራል፡፡ በአንጻሩ ደግሞ ክፉ ማድረግና የእግዚአብሔር ትእዛዝ መዘንጋት ወደ ጥፋት እንደሚመራና ከእግዚአብሔርም ጋር እንደሚያቈራርጥና መጨረሻውም እንደ በረሓ አበባ በፍጥነት መርገፍ እንደሆነ ያስተምራል(መዝ 37፡ 20)፡፡
👉ካህናት የቤተ መቅደስን ደረጃዎች ሲወጡ የሚዘምሩአቸው የመዐረግ መዝሙሮች (መዝ 120-134)፡፡
እነዚህ መዝሙሮች በተለያየ ጉዳይ ላይ የሚያተኩሩ ናቸው፡፡ የእነዚህ መዝሙሮች አብዛኛው ትኩረት የእግዚአብሔር ጠባቂነት ለማግኘት ቢሆንም ሌሎች አሳቦችም በመዝሙሮች ውስጥ በጸሎትና በልመና መልክ ተካተዋል፡፡
👉ሃሌሉያ ብለው የሚጀምሩት የሃሌል መዝሙሮች (የስብሐት መዝሙሮች) (መዝ 111-113፤ 146፤ 148-150)፡፡
እነዚህ መዝሙሮች ከሌላው ክፍል የሚለዩበት ዋናው ምክንያት ገና ከመዝሙሩ ጅማሬ እግዚአብሔርን ያመስግናል፡፡ መዝሙሮቹ ሲጀምሩ "እግዚአብሔር ይመስገን" ወይም "እግዚአብሔርን አመስግኑት" በማለት ይጀምራሉ፡፡ ስለዚህ መዝሙሮቹ የምስጋና መዝሙሮች ተብለው ይታወቃሉ፡፡
✔️✔️የዳዊት ገቢር
#ለአቃቤ_ዕርስ
❤️መዝሙር፭ #ቃልየ፧አጽምዕ፧እግዚኦ፧ወለቡ፧ጽራሕየ.... ከሚለው ጀምሮ ሙሉውን መድገም
#ገቢሩ..በየብስም,ባሕርም,በመንገድም እህል ሳትቀምስ በቅባ ቅዱስ ,በሜሮን,ውሀ ባልነካው ቅቤ ..በማንኛውም ቅባት ላይ ፯ ጊዜ ደግመህ ተቀባ #ከሞት ይጠብቅሀል
እንዲሁ #ለራስ_ምታት በቅቤ ፯ ጊዜ ደግመህ ተቀባ ።
#አይኑን_ለታመመ
❤️መዝሙር ፮
#እግዚኦ፣በመዓትከ፣ኢትቅሥፈኒ፣ወበቅሠፍትከ፣ኢትገሥጸኒ.... ከሚለው ጀምሮ ሙሉውን መድገም
#ገቢሩ .. መዝሙሩን ፯ ጊዜ ደግሞ ፅፎ መያዝ እንዲሁ በቅቤ ፯ ጊዜ ደግሞ የታመመውን አይን መቀባት ያድናል ።
#ደግሞም ለምትፈራው ነገር ሁሉ ከቤት ሳትወጣ ማንኛውንም ሽት ቤት ሳትጠቀም ከሰው ሳትነጋገር የምትፈራውን ሰው ስም ከነእናቱ ስም እየጠራህ ፯ ጊዜ ድገም ከእሱ ትድናለህ ።
#አስማት_ለተዋለበት_የአጋንንት_ቁራኛ_ለያዘው_ሰው
❤️መዝሙር ፯
#እግዚኦ፣አምላኪየ፣ብከ፣ተወከልኩ፣ኢትግድፈኒ....ከሚለው ጀምሮ ሙሉውን መድገም ።
#ገቢሩ .. ፀሀይ ከማታየው ጉድጓድ ውሀ ቀድተህ ከዕለቱ ከዕለቱ ሐፁረ መስቀል ፣ አርድእት ፣ ባርቶስ ጋር ፰ ቀን ፯ ፯ጊዜ ደግመህ አጥምቀው በእግዚአብሔር ቸርነት ይድናል ። ይህንንም ስታደርግ ደርግ ልጅና ከብት ማንኛውንም ሰው ከሌለበት ሜዳ ነው ። ከቤትም ከመንገድም አትድገም
#እንደዚሁ ባሏ ለጠላት ሴት በቅቤ ፯ ጊዜ ደግመህ ሰውነቷን ትቀባ ባሏ ይወዳታል ።
#ለታመሙ_ሕፃናት
❤️መዝሙር ፰
#እግዚኦ፣እግዚእነ፣ጥቀ፣ተሰብሐ፣ስምከ፣በኩሉ፣ምድር..ከሚለው ጀምሮ ሙሉውን መድገም ።
#ገቢሩ መዝሙሩን ጽፈህ አሲዘው ይፈወሳል ።
#እንዲሁ ለታሰረ ሰውም በኅብስት ላይ ጽፈህ ስጠው በእግዚአብሔር ቸርነት ይፈታል
#እንዲሁ በዝርግ ሳህን ላይ ጽፈህ በዓሣ መረብ ከተህ ከባህር ብትጥለው ብዙ አሳ ይያዝልሃል ።
#እንዲሁ ለገበያ በእንቧጮ አርጩሜ ፯ ጊዜ ደግመህ የምትሸጠውን እቃ ፯ ጊዜ ብትመታው ይሸጣል
#እንዲሁ ጥሬ ጨው በማር ለውሰህ ፯ ጊዜ ደግመህ ብትበላ ከሰው ጋር በፍቅር እና በሰላም ለመኖር ያስችልሃል ።