Ministry of education®


Гео и язык канала: Иран, Фарси
Категория: не указана


Похожие каналы

Гео и язык канала
Иран, Фарси
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ጎንደር ዩኒቨርሲቲ 70ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ማክበር ጀምሯል።

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 70ኛ ዓመት እና የዩኒቨርሲቲው አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ማስተማሪያ ሆስፒታል 100ኛ ዓመት ክብረ-በዓል የመክፈቻ ሩጫ ውድድር በጎንደር ከተማ ተካሒዷል።

ዩኒቨርሲቲው በህክምናና ጤና ሳይንስ ዘርፍ ዕውቀትን የተካኑ ባለሙያዎችን በማፍራት ለሀገሪቱ የላቀ አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ እንደሚገኝ በኹነቱ ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል።

በቀጣይ ሁለት ዓመታት ራስ-ገዝ ከሚሆኑ 10 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ጎንደር ዩኒቨርሲቲ አንዱ ነው።

ኢትዮጵያውያን ሐኪሞች እንዲኖሩ ታስቦ በ1947 ዓ.ም የተመሰረው ዩኒቨርሲቲው፤ ከ100 ሺህ በላይ ምሩቃንን ማፍራቱን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አስራት አፀጸወይን (ዶ/ር) ገልፀዋል።

የምስረታ በዓሉ እስከ ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ድረስ የሚከበር ሲሆን፤ ለተቋሙ ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ግለሰቦች ዕውቅና መስጠትን ጨምሮ ከ20 በላይ ኹነቶች እንደሚከናወኑ ይጠበቃል።

   🙏Share share🙏
👇👇ለተጨማሪ መረጃ👇👇

https://t.me/Temhert_Minister1
https://t.me/Temhert_Minister1
https://t.me/Temhert_Minister1


ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለተቋሙ አስተዋፅኦ ላደረጉ ግለሰቦች የሕንፃ፣ የመንገድ እና የአዳራሽ ስያሜ ሊያደርግ ነው፡፡

የዩኒቨርሲቲው ሕንፃ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲገነባ መሬታቸውን ለሰጡ ግለሰቦች የመታሰቢያ ቀን እንደሚሰየምላቸው ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 70ኛ ዓመት እና የዩኒቨርሲቲው አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 100ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አከባበርን አስመልክቶ የተቋሙ ፕሬዝዳንት አስራት አፀደወይን (ዶ/ር) ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የምስረታ በዓሉ በስፖርታዊ ውድድር፣ የአዳዲስ መሠረተ ልማቶች ግንባታ በማስጀመር፣ ነጻ የማኅበረሰብ አገልግሎት በመስጠት እና የተለያዩ ፕሮጀክቶች በማስመረቅ እንደሚከበር ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል፡፡

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ 11 ኮሌጆች፣ 12 የምርምር ማዕከላት እንዲሁም አንድ የማስተማሪያ ሆስፒታልና የእንስሳት ሕክምና ሆስፒታል አለው። #ሪፖርተር

   🙏Share share🙏
👇👇ለተጨማሪ መረጃ👇👇

https://t.me/Temhert_Minister1
https://t.me/Temhert_Minister1
https://t.me/Temhert_Minister1


#BongaUniversity

በ2017 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት የካትቲ 1 እና 2/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➭ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➭ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➭ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቅያ ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➭ ስድስት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ፣
➭ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

   🙏Share share🙏
👇👇ለተጨማሪ መረጃ👇👇

https://t.me/Temhert_Minister1
https://t.me/Temhert_Minister1
https://t.me/Temhert_Minister1


#WallagaUniversity

በ2017 ዓ.ም በመደበኛ ፕሮግራም ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) ወለጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ ጥር 19 እና 20/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦

➭ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ስማችሁ ከ A-M የሚጀምር በዋናው ካምፓስ ነቀምቴ
➭ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ስማችሁ ከ N-Z የሚጀምር ሻምቡ ካምፓስ
➭ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ስማችሁ ከ A-H የሚጀምር በዋናው ካምፓስ ነቀምቴ
➭ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ስማችሁ ከ I-Z የሚጀምር በጊምቢ ካምፓስ

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➭ ከ8-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➭ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ
➭ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ

   🙏Share share🙏
👇👇ለተጨማሪ መረጃ👇👇

https://t.me/Temhert_Minister1
https://t.me/Temhert_Minister1
https://t.me/Temhert_Minister1


ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለት የጆርናል ውጤቶቹን ለህትመት አብቅቷል፡፡

Salale Journal of Social and Indigenous Studies (SJSIS) እና Horn African Journal of Health and Biomedical Sciences (HAJHBS) የተሰኙት የምርምር ጆርናሎች በሀርድ ኮፒ መታተማቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

ጆርናሎቹ በተለያዩ የማኅበራዊ እና አገር-በቀል ጥናቶች እንዲሁም የጤና እና ባዮ-ሜዲካል ምርምሮች ላይ ትኩረት ያደርጋሉ።

   🙏Share share🙏
👇👇ለተጨማሪ መረጃ👇👇

https://t.me/Temhert_Minister1
https://t.me/Temhert_Minister1
https://t.me/Temhert_Minister1


#ይመዝገቡ

የመውጫ ፈተና (Exit Exam) በድጋሜ ለመውሰድ ፍላጎት ያላቸው አመልካቾች ምዝገባ ነገ ረቡዕ ጥር 14/2017 ዓ.ም ያበቃል፡፡

ለመመዝገብ 👉 https://exam.ethernet.edu.et

➫ የመፈተኛ User Name እና Password በመመዝገቢያ ፖርታል በኩል የሚላክ ይሆናል።
➫ የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 500 በቴሌብር በኩል ብቻ መፈፀም ይኖርባችኋል፡፡
➫ ምዝገባ ማድረግ የሚቻለው በተጠቀሱት የምዝገባ ቀናት ብቻ ነው፡፡

   🙏Share share🙏
👇👇ለተጨማሪ መረጃ👇👇

https://t.me/Temhert_Minister1
https://t.me/Temhert_Minister1
https://t.me/Temhert_Minister1


#ማስታወሻ

በሠመራ ዩኒቨርሲቲ ለ2017 የአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ነገ ረቡዕ ጥር 14/2017 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል፡፡ ምዝገባ ጥር 15 እና 16/2017 ዓ.ም ይከናወናል፡፡

   🙏Share share🙏
👇👇ለተጨማሪ መረጃ👇👇

https://t.me/Temhert_Minister1
https://t.me/Temhert_Minister1
https://t.me/Temhert_Minister1


#NGAT

ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ሲሰጥ ውሏል፡፡

በ2017 ዓ.ም ሁለተኛ ሴሚስተር የድኅረ-ምረቃ ትምህርት ለመከታተል የተመዘገቡ አመልካቾች ፈተና ትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው መርሐግብር መሰረት በተለያዩ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ዛሬ ተሰጥቷል፡፡

ምስል፦ ዲላ ዩኒቨርሲቲ፣ ወራቤ ዩኒቨርሲቲ፣ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ፣ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ

   🙏Share share🙏
👇👇ለተጨማሪ መረጃ👇👇

https://t.me/Temhert_Minister1
https://t.me/Temhert_Minister1
https://t.me/Temhert_Minister1


#AksumUniversity

በ2017 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) አክሱም ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ጥር 15 እና 16/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ፣ አክሱም ከተማ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ ክፍል ፈተና የወሰዳችሁበት ማስረጃ ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ፈተና የወሰዳችሁበት ማስረጃ ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ2ኛ ደረጃ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➫ 3×4 የሆነ ስድስት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ የመኝታ አልባሳት እና የስፖርት ትጥቅ፣
➫ ማንነታቸሁ የሚገልፅ የታደሰ መታወቂያ፡፡

   🙏Share share🙏
👇👇ለተጨማሪ መረጃ👇👇

https://t.me/Temhert_Minister1
https://t.me/Temhert_Minister1
https://t.me/Temhert_Minister1


#NGAT

ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) እየተሰጠ ነው፡፡

በ2017 ዓ.ም ሁለተኛ ሴሚስተር የድኅረ-ምረቃ ትምህርት ለመከታተል የተመዘገቡ አመልካቾች ፈተና ትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው መርሐግብር መሰረት በተለያዩ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ዛሬ ጠዋት መሰጠት ጀምሯል፡፡

ምስል፦ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ፣ ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ፣ ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ

   🙏Share share🙏
👇👇ለተጨማሪ መረጃ👇👇

https://t.me/Temhert_Minister1
https://t.me/Temhert_Minister1
https://t.me/Temhert_Minister1


#Update

ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለመፈተን የተመዘገቡ አመልካቾች ከፈተና ፕሮግራም ጋር ተያይዞ ማስተካከያ ማድረጉን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

አመልካቾች ዝርዝር መረጃውን https://ngat.ethernet.edu.et ላይ በመግባት ማየት እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ ጠቁሟል፡፡

ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ነገ ረቡዕ ጥር 7/2017 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

ምዝገባ ያደረጋችሁበትን አድራሻ ማለትም https://ngat.ethernet.edu.et በመጠቀም የፈተና ፕሮግራም እና የመፈተኛ መግቢያ ቲኬታችሁን ማግኘት ትችላላችሁ።

ተፈታኞች ወደፈተና ማዕከል ስትሔዱ ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ እና የመፈተኛ Entrance Ticket መያዝ ይኖርባችኋል። ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዞ ወደፈተና ማዕከል መግባት ፈፅሞ የተከለከለ መሆኑም ተገልጿል፡፡

   🙏Share share🙏
👇👇ለተጨማሪ መረጃ👇👇

https://t.me/Temhert_Minister1
https://t.me/Temhert_Minister1
https://t.me/Temhert_Minister1


#ጥቆማ

በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ በተለያዩ የትምህርት መስክ አመልካቶችን አወዳድሮ በመምህርነት በቋሚ ኮንትራት መቅጠር ይፈልጋል፡፡

➤ የሥራ መደብ፦ በተለያዩ የትምህርት ክፍሎች
➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 116
➤ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ ከ2ኛ ዲግሪ ጀምሮ
➤ የሥራ ቦታ፦ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ
➤ የመመዝገቢያ ጊዜ፦ እስከ ጥር 16/2017 ዓ.ም
➤ የምዝገባ ቦታ፡- አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ የብቃትና ሰው ሀብት አስተዳደር ቡድን 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 51

Note:
አመልካቾች ለምዝገባ ስትሔዱ የ8ኛ ክፍል ሰርተፍኬት፣ የ12ኛ/10ኛ ክፍል ስርተፍኬት፣ ከመጀመሪያ ዲግሪ ጀምሮ ያሉ ሰርቲፊኬት እና ትራንስክሪፕት ዋናውና አንድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡

በተጨማሪም የታደሰ የሙያ ፍቃድ ማቅረብ የሚጠበቅባችሁ ሲሆን፤ በውጪ ሀገራት ትምህርታችሁን የተከታተላችጁ አመልካቾች በህግ ሥልጣን በተሰጣቸው አካላት የትምህርት ደረጃ አቻ ግመታ ሰነድ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡

   🙏Share share🙏
👇👇ለተጨማሪ መረጃ👇👇

https://t.me/Temhert_Minister1
https://t.me/Temhert_Minister1
https://t.me/Temhert_Minister1


Репост из: MOON LAPTOPS

Показано 13 последних публикаций.