እንደዚሁም ነቢያችን ሙሐመድ ኢብን ዓብዲላህ صلى الله عليه وسلم ተውሒድን ያረጋገጡ በእሱም የኖሩና በሱ ወደ አላህ ከተቃረቡ ሰዎች ውስጥ ዋናውና ትልቁ እርሳቸው ናቸው። አላህም ከጂንና ሰዎች ተንኮል ጠበቃቸው። አላህ ለነቢዩ ሙሐመድ صلى الله عليه وسلم አላቸው
يَـٰٓأَيُّهَا ٱلرَّسُولُ بَلِّغۡ مَآ أُنزِلَ إِلَيۡكَ مِن رَّبِّكَۖ وَإِن لَّمۡ تَفۡعَلۡ فَمَا بَلَّغۡتَ رِسَالَتَهُۥۚ وَٱللَّهُ يَعۡصِمُكَ مِنَ ٱلنَّاسِۗ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَهۡدِي ٱلۡقَوۡمَ ٱلۡكَٰفِرِينَ
አንተ መልክተኛ ሆይ! ከጌታህ ወዳንተ የተወረደውን አድርስ። ባትሠራም መልእክቱን አላደረስክም። አላህም ከሰዎች ይጠብቅሃል። አላህ ከሓዲዎችን ሕዝቦች አያቀናምና።
አላህ ሱ.ወ. እንዲህ ይላል፡
يَـٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِيُّ حَسۡبُكَ ٱللَّهُ
አንተ ነቢዩ ሆይ! አላህ በቂህ ነው።
አላህም ለነቢዩ صلى الله عليه وسلم ቃልኪዳኑን ፈፀመላቸው፤ የቁረይሽ ኩፋሮችን ተንኮል መለሰላቸው። በዋሻው ውስጥ ጠበቃቸው፤
لا تَحْزَنْ إِنَّ اللَّهَ مَعَنَا አትዘን አላህ ከእኛ ጋር ነው አሉ። ከየሁዶች ተንኮል ሰላም አደረጋቸው፤ እሱንም አሳወቃቸው፤ ከተመረዘ የበግ ስጋም አዳናቸው። ረሱሉላህ صلى الله عليه وسلم ከባልደረቦቻቸው ጋር ከአንድ ዘመቻ የተመለሱ ጊዜ እሾካማ የሆነ ብዙ ዛፍ ያለበት አንድ ሸለቆ ወስጥ ቀይሉላ[2] ሰዓት ደረሰና ረሱል صلى الله عليه وسلم አረፍ አሉ፤ ሶሐቦቹም በየዛፉ ስር ጥላ ፍለጋ ተበታተኑ፤ ረሱልም صلى الله عليه وسلم አንድ ትልቅ ዛፍ ስር አረፉ፤ ሰይፋቸውን ዛፉ ላይ አንጠለጠሉ፤ ሁሉም እንቅልፍ ተኙ። ከሙሽሪኮቹ የሆነ አንድ ሰው መጣና በነብዩ صلى الله عليه وسلم ራስ በኩል ሰይፋቸውን ይዞ ቆመ፤ ይህ ሙሽሪክ በረሱል صلى الله عليه وسلم ላይ ሰይፋቸውን እስኪመምዘዝ ድረስ ሰርጎ ገባ፤ ረሱሉላህ صلى الله عليه وسلم ብቻቸውን ሆነውውስጥ ከኔ የሚከላከልልህ ማነው አላቸው። ረሱል صلى الله عليه وسلم ጋር ሰይፍ የለም፤ ሰይፉ ይህ ሙሽሪክ እጅ ስር ሆኗል። ሁለቱ ብቻቸውን ናቸው። ”ከኔ የሚከላከልልህ ማነው?“ አለ። ነብዩም صلى الله عليه وسلم ተውሒድን ሙሉ የሆነ ማረጋገጥን ያረጋገጡ፣ በልባቸውም የአላህ ትልቅነት ጠልቆ የሰረፀባቸው እርሳቸው ናቸውና “አላህ” አሉት፤ በዚህ ጊዜም ሰይፉ ከእጁ ወደቀ። አላህ ጠበቃቸው። ረሱሉላህ صلى الله عليه وسلم ያዙትና ”ከኔ የሚከላከልልህ ማነው?“ አሉት። ”መልካም ያዥ ሁን!“ አላቸው። ”ላኢላሀ ኢለላህ ብለህ ትመሰክራለህ?“ አሉት። ”አይ አልመሰክርም፤ ነገር ግን ላልዋጋህና ከሚዋጉህም ሰዎች ጋር ላለመሆን ቃል እገባልሀለሁ“ አላቸው። ነቢዩም صلى الله عليه وسلم ለቀቁትና ወደ ባልደረቦቹ ሄዶ ”ከሰዎች ሁሉ በላጭ ከሆነ ሰው ጋ ነው የመጣሁት“ አለ። ችግርና ፈተና በበረታበትና በአደጋ ጊዜ የአንቢያኦች አካሄዳቸው (ሚንሀጅ) ነው። በተውሒድ ይጠጋሉ፤ በሱም ወደ አላህ ይቃረባሉ። ይህንን የመጀመሪያዎቹ ሙሽሪኮችም አውቀውታል፤ ከአስቸጋሪ ሁኔታዎችና አደጋዎች ለመዳን ባላቸው የተውሒድ ቅሪት ይጠበቁ ነበር። የመጀመሪያዎቹ ሙሽሪኮች በደህና ጊዜ ያሻርኩና በችግርና በስጋት ጊዜ ከችግሩ ለመውጣትና ጉዳት በደረሰባቸው ጊዜ እርዳታ ለመጠየቅ ግን የሚያውቁት የተውሒድ ቅሪት በመኖሩ በተውሒድ ይጠጋሉ። አላህ ሱ.ወ. አለ
حَتَّىٰٓ إِذَا كُنتُمۡ فِي ٱلۡفُلۡكِ وَجَرَيۡنَ بِهِم بِرِيحٖ طَيِّبَةٖ وَفَرِحُواْ بِهَا جَآءَتۡهَا رِيحٌ عَاصِفٞ وَجَآءَهُمُ ٱلۡمَوۡجُ مِن كُلِّ مَكَانٖ وَظَنُّوٓاْ أَنَّهُمۡ أُحِيطَ بِهِمۡ دَعَوُاْ ٱللَّهَ مُخۡلِصِينَ لَهُ ٱلدِّينَ لَئِنۡ أَنجَيۡتَنَا مِنۡ هَٰذِهِۦ لَنَكُونَنَّ مِنَ ٱلشَّـٰكِرِينَ ٢٢ فَلَمَّآ أَنجَىٰهُمۡ إِذَا هُمۡ يَبۡغُونَ فِي ٱلۡأَرۡضِ بِغَيۡرِ ٱلۡحَقِّۗ
በመርከቦችም ውስጥ በሆናችሁና በእነርሱም በመልካም ነፋስ በርሷ የተደሰቱ ኾነው (መርከቦቹ) በተንሻለሉ ጊዜ ኀይለኛ ነፋስ ትመጣባታለች። ከየስፍራውም ማዕበል ይመጣባቸዋል። እነሱም (ለጥፋት) የተከበቡ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ። (ያን ጊዜ) አላህን ከዚህች (ጭንቀት) ብታድነን በእርግጥ ከአመስጋኞቹ እንሆናለን ሲሉ ሃይማኖትን ለርሱ ብቻ ያጠሩ ሆነው ይለምኑታል። በአዳናቸውም ጊዜ እነሱ ወዲያውኑ ያለ አግባብ በምድር ላይ ወሰን ያልፋሉ።
አላህ ሱ.ወ. ይላል
فَإِذَا رَكِبُواْ فِي ٱلۡفُلۡكِ دَعَوُاْ ٱللَّهَ مُخۡلِصِينَ لَهُ ٱلدِّينَ فَلَمَّا نَجَّىٰهُمۡ إِلَى ٱلۡبَرِّ إِذَا هُمۡ يُشۡرِكُونَ
በመርከቦች ውስጥ በተሳፈሩ ጊዜም አላህን መገዛትን ለእርሱ ብቻ ያጠሩ ኾነው ይጠሩታል። ወደ የብስ (በማውጣት) ባዳናቸው ጊዜም ወዲያውኑ እነርሱ (ጣዖትን) ያጋራሉ፡ ፡
ፊርዓውን እንኳን ሳይቀር ባህሩ ባሰመጠው ጊዜ ወደ ተውሒድ በመጠጋት የመጀመሪያዎቹን ሙሽሪኮችን ፈለግ ከመከተል አልወጣም። አላህ አለ
حَتَّىٰٓ إِذَآ أَدۡرَكَهُ ٱلۡغَرَقُ قَالَ ءَامَنتُ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا ٱلَّذِيٓ ءَامَنَتۡ بِهِۦ بَنُوٓاْ إِسۡرَـٰٓءِيلَ وَأَنَا۠ مِنَ ٱلۡمُسۡلِمِينَ
መስጠምም ባገኘው ጊዜ፡- «አመንኩ። እነሆ ከዚያ የእስራኤል ልጆች በርሱ ከአመኑበት በስተቀር ሌላ አምላክ የለም። እኔም ከታዛዦቹ ነኝ» አለ።
ይሁንና ለፊርዓውን የተሰጠው የተውበትና የማመን ጊዜ አልፎ የነበረ ከመሆኑ ጋር አላህ በድኑን አወጣው። አላህ እንዳለው
فَٱلۡيَوۡمَ نُنَجِّيكَ بِبَدَنِكَ لِتَكُونَ لِمَنۡ خَلۡفَكَ ءَايَةٗۚ وَإِنَّ كَثِيرٗا مِّنَ ٱلنَّاسِ عَنۡ ءَايَٰتِنَا لَغَٰفِلُونَ
ዛሬማ ከኋላህ ላሉት ተዓምር ትሆን ዘንድ በድን ሆነህ (ከባሕሩ) እናወጣሃለን (ተባለ)። ከሰዎችም ብዙዎቹ ከተዓምራታችን በእርግጥ ዘንጊዎች ናቸው።
የአላህ ባሮች ሆይ በአላህ አዛኝነትና ጥበቃ እርግጠኛ ሁኑ፤ የአላህን አንድነት (ተውሒድ) አረጋግጡ፤ በችግርም ጊዜ በሱ ወደ አላህ (ተወሱል አድርጉ) ተቃረቡ። የሀዘናችሁን መወገድ ታያላችሁ። በጣዖት በመካድ፣ በአላህ በማመን፣ በወላእ ወልበራእ ወደ አላህ ተቃረቡ። የዚህን ጊዜ የዱዓችሁን ምላሽ ማግኘት ውጤትና ፍጥነቱንም ታያላችሁ። የእነዚያ መሀይማን ሙሽሪኮች ችግራቸውን ለማስወገድ ተውሂድ ከሚያመጣው ውጤት አፈንግጠው ሽርክን ወደ አላህ መቃረቢያ (ተወሱል) ማድረጋቸው የሚገርም ነው፣ በመከራ ጊዜ ወደ ቀብርና ደሪሆች መሄዳቸውና ከአላህ ውጪ ያለን አካል እንዲደርስላቸው እርዳታ (ኢስቲጋሳ) መጠየቃቸው አስገራሚ ነው። እርዳታን ከመነፈግ በአላህ እንጠበቃለን።