የአዳም ጤና/ጤና -አዳም
የጥርስ ቁርጥማት ስቃይ የቀመሰ ማነው?
#በጥርስ መቦርቦር ምክንያት ከፍተኛ እና አስቀያሚ ከሆነው የጥርስ ቁርጥማት ጋር በዚህ ግዜ ፍልምያ ገጥመዋል?
#ወድያውኑ ወደጓሮዎ በመሄድ የጤና-አዳም ፍሬን ይፈልጉ እንዲሁም ይፈወሱ።
♦የጥርስ መቦርቦር እንዴት ይከሰታል?
#በጥርስ ላይ ተለጥፈው የሚቀሩ ምግቦች ካልተፀዱ ይከማቹና የባክቴሪያዎች መራቢያ እና ምግብ ይሆናሉ።
#ባክቴሪያዎች በሚመገቡ ጊዜ ከውስጣቸው አሲድን ይረጫሉ፣ ይህም ጥርሳችን እንዲቦረቦርና እንዲበሰብስ ያደርጋል።
#ጥርስን በሚገባና በመደበኛ ሁኔታ አለማፅዳት
#ጣፋጭነት የበዛባቸው ምግቦች ማዘውተር
#የፍሎራይድ እጥረት መኖር
#የስኳር ህመም ተጠቂ መሆን
#በህመም ወይንም በተለያዩ መድሀኒቶች ምክንያት የአፍ ድርቀት ሲኖር
#ሲጋራን ማጤስ ናቸው።
♦የጥርስ መቦርቦር የሚያስከትላቸው ምልክቶች!
#የጥርስ ህመም ስሜት
#በተጎዳው ጥርስ አካባቢ የድድ ማበጥ
#መጥፎ የሆነ የአፍ ጠረን መኖር
#በጥርስ ላይ ነጭ፣ ግራጫ፣ ቡኒ ወይንም ጥቁር ቀለማት የያዙ የተቦረቦሩ ቦታዎች መኖር ናቸው።
♦የጥርስ መቦርቦርን እንዴት መከላከል ይቻላል?
#ጥርስ በቀን ውስጥ ቢያንስ ሁለት ጊዜ (ከቁርስ በኃላ እና ከመተኛትዎ በፊት) የፍሎራይድ ኬሚካል ባለው የጥርስ ሳሙና መታጠብ።
#በማንኛው ግዜ ምግብ ከተመገቡ በኃላ አፍዎን በንፁህ ውሀ በሚገባ መጉመጥመጥ!
#ከእንቅልፍ በፊት ጥርስዎን ከታጠቡ በኃላ ምንም አይነት ምግብ አለመመገብ!
#ጣፋጭ የበዛባቸው ምግቦችን ከምግብ ፕሮግራም ውስጥ ማስወገድ!
#በጥርስ መቦርቦር እንዲሁም በሌላ ምክንያት ለሚከሰት የጥርስ ቁርጥማት መፍትሔ
♥የአዳም-ጤና /የጤና-አዳም ፍሬ
#ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያለው የጤና አዳም-ፍሬ በአብዛኞቻችን ቤት የማይጠፋው ጤና አዳም የጥርስ ቁርጥማት መፍትሔ መሆኑን ባለማወቃችን ብዙ ተሰቃይተን ይሆናል።
#የጤና አዳም ፍሬ በእርጥቡም/በደረቁም ፯ ራስ ፍሬ አዘጋጅተው በሚቆረጥሞት ክፍል ለ 10 ደቂቃ ያክል ማኘክ/ማላመጥ ውኃውን እየተፉ ይሁን።
#ወድያዉኑ ከከፍተኛ የጥርስ ቁርጥማት ይፈወሳሉ።
#ማሳሰብያ
#ይህ ፈውስ አሰጣጥ በተደጋጋሚ ካልተጠቀሙት በቀር ዘላቂ እና ፍፁም የሆነ መፍትሔ ላይሰጥ ይችላል።ከጊዝያዊ የጥርስ ቁርጥማት ግን ፍፁም ፈውስ ሰጪ መፍትሔ ነው።
♦ቢቻላችሁ የጓሮ ተክል በሆነው የጤና- አዳም ፍሬ የጥርስ ቁርጥማት ማዳንን እንደሚቻል ለመልካሙ እና ደጉ ህዝባችን ይደርስ ዘንድ የአነባችሁትን ለማህበረሰቡ ማሳወቅ አይዘንጉ።
መሪጌታ አምደብርሃን ይትባረክ የባህል ህክምና
♥የቀደምት አባቶቻችንን እውቀት እና ጥበብ ሳይበረዝ እንደወረደ ይቀርባል። የአያቶቻችን የእጽዋት ጥበብ፣ በህይወትዎ ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው፣ ክፉ መናፍስትን እንዴት ማራቅ እንደምንችል፣ የብራና መጽሐፍት እና ጥቅማቸው በዚ ይዳሰሳሉ።
#0918487073
#0920253444
መልእክት ለምስቀመጥ
@mergetaam የሚከተሉትን ሰው ጠንቅቀው ይወቁ !!!