የኳታር አሚር ሸይኽ ተሚም ቢን ሀሚድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት በሶሪያ ዋና ከተማ ደማስቆ በዛሬው ዕለት መግባታቸው የተገለፀ ሲሆን ጊዜያዊ የሶሪያ መንግስት ፕሬዝዳንት አህመድ አል ሻራ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ኳታር እና ሶሪያ በሚኖራቸው ግንኙነት ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉም ተብሎ ይጠበቃል። በሶሪያ ከበሽር አላሳድ መንግስት መውደቅ በኋላ አሚሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ደማስቆ መግባታቸውም ታውቋል።
ሶሪያ ወደ ዘላቂ ሰላም እንድትመጣ በትላንትናው ዕለት ጊዜያዊ የሶሪያ መንግስት ፕሬዝዳንት ሆነው ከተሾሙት አህመድ አልሻራ ጋር ውይይት እንዲሚያደረጉም ተገልጿል።
ኳታር ከቱርክ ቀጥሎ በሶሪያ የሚገኘውን ኤምባሲዋን የከፈተች ሀገር ስትሆን ሶሪያን መልሶ ለመገንባት በሚደረገው ሂደት ላይ አስፈላጊውን እገዛ እንደምታደርግ የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በትላንትናው ዕለት አስታውቋል።