○◎ከግጥም ማዓድ (ጭውውት)
◦◦◎○
✅ከሀገር ሀገር እውቀትን በመፈለግ የሚከራተተው ደረሳና ዘመናዎነት ያጠቃው ወጣት ያደረጉት ቁም ነገር አዘል ጭውውት በግጥም መልክ።
• ⏩⏩ደረሳው እና ወጣቱ⏪⏪
ደረሳው፦አሰላሙአለይኩም ወንድሜ እንደምነህ፣
ጠፋህ እሳ ምነው፤ መስጅድም አላይህ።
ወጣቱ፦ ሃይ ደረሴ እንዴት ነሽ፤ ሰላም ነሽ፣
ደግሞ አምሮብሻል ፤ በዚህ ሰዓት ወዴት ነሽ።
ደረሴ፦ ምነው የኔ ወንድም?፤
በኢስላም ሰላምታ መልስልኝ እንጂ፣
የፈረንጁ እንደሆን፣
ላንተም ሆነ ለኔ ለማንም አይበጅ።
ወጣቱ፦ ኡፍ አንች ደግሞ ፤ ስታይል አታርፊም፣
በቃ ደስ ይበለሽ ዋአለይኩም ሰላም።
ደረሴ፥ አዎ እንደዚህ ነው ፤ ተብሎ ሚመለሰው፣
ይሄንኛው እኮ ነው ፤ አስር አጅር ያለው።
ወጣቱ፦ በቃ ደስ እንዳለሽ ፤ አንቺን እንደተመቸሽ፣
ደረሳ ነሽና፤ እስታይል ሙድ አይገባሽ።
ደረሴ፦ ምነው የኔ ወንድም? ሴት መሰልኩህ እንዴ፣
አንቺ አንቺ ምትለኝ፤ ሴት እመስላለሁ እንዴ?
ወጣቱ፦ አቦ ለምዶብኝ ነው፤ አንቺ የምልህ።
በቃ ካሁን በኋላ፤ አንተ ነው ምልህ።
ደረሴ፦ ታዲያ ምነው ጠፋህ? መስጅድም አላይህ፣
መድረሳም አትመጣ፤ ምነው ምን ገጠመህ?
ወጣቱ፦ ኦማይጋድ! ኦማይጋድ! ደረሴ አየሃት?
አቤት ቁንጅና! አቤት ውበቷ፤
እንዴት ቀሽት ልጅ ናት።
ደረሴ፦ ምነው የኔ ወንድም ፤ ምን ተመልክተህ ነው?
አኡዙ ቢላሂ፤ እይ ያልከኝ ይሄን ነው?
ወጣቱ፦ አወና ደረሴ፤ እስኪ እያት አታምርም?
ዉበት ቁንጅናዋ ፤ አፍዞ አያስቀርም?
ደረሴ፦ አቦ ወግድልኝ ምን አይነት ወስዋስ ነው፣
አጅ ነቢ መመልከት፤ በኢስላም ሀራም ነው።
ወጣቱ፦ ቋይ ተፈኩር ማድረግ፤ ምን ችግር አለበት?
ዉበቷን እያዩ፤ ሱብሃነላህ ማለት።
ደረሴ፦ ታዲያ ለተፈኩር፤ ስንት መንገድ እያለህ፣
አላህ በሐረመው፤ ምን ችክ ትላለህ።
ወጣቱ፦ ቆይ ምን ችግር አለው፤
እኔ እሷን ብመለከት፣
ቁንጅናዋን ባደንቅ፤
ምን ጥፋት አለበት?
ደረሴ፦ እስኪ መልስልኝ፤ አንዴ ልጠይቅህ፣
ደስ ይለሃል እንዴ፤ እህትህን ቢያዩብህ?
ወጣቱ፦ ኧረ በፍፁም፤
በጭራሽ አልፈቅድም፣
ማንም ለከስካሳ እህቴን እንዲለክፋት፣
በፍፁም አልሻም።
ደረሴ፦ አየህ የኔ ወንድም፤ እሷም ወንድም አላት፣
በፍፁም የማይፈቅድ ፤ አንተስ እንድትለክፋት።
ወጣቱ፦ እኔ መች አወቅኩኝ፤ መች ተገነዘብኩኝ፣
ስሜቴን ብቻ እንጂ፤ ሌላ መች አየሁኝ።
ደረሴ፦ ለሌላ አታድርግ ፤ ላንተ ማትወደውን፣
ሰው አይወድምና፤ አንተ ምትጠላውን።
ወጣቱ፦ በቃ እተዋለው፤ እንግዲህ፣
ሁለተኛ አላይም፤ በቃ ከእንግዲህ።
ደረሴ፦ አዎ የኔ ወንድም፤ እንዲህ ነው ሚባለው፣
እንደዚህ እንዳንተ ምክር ሚሰማን ነው፤
አላህ የሚወደው።
ወጣቱ፦ 👉በአላህ ደረሴ ፤ ከልብ አፉ በለኝ፣
በተናገርኩት ነገር፤ እንዳትቀየመኝ።
ደረሴ፦ ኧረ እኔ ትቻለው፤ ብዩ አፈውቱሊላህ፣
ባይሆን አንተ ቶብት፤ በል አስተግፊሩላህ።
ወጣቱ፦ ጌታዩ አጥፍቻለው፤ ይቅር በለኝ እባክህ፣
ቶብቻለሁና፤ እያኝ በእዝነትህ።
ደረሴ፦ አሁን ሰላት ደርሷል፤ ሀያ መስጅድ እንሂድ፣
ዉዱዕ እናድርግና ፤ በጀመዓ እንስገድ።
🔀ያን ገራገር የኢልም ፈላጊ ደረሳ አላህ ይዘንለት ለወጣቱ መመራት ሰበብ ነውና።
✅አንተ ውዱ ወንድሜ ሆይ የአይሁዳን ሱና ሳይሆን የነብዩን ሱና ተከተል አይንህን ስበር።
✅አንቺ ዉዱዋ እህቴ ሆይ እራስሽን በሒጃብ ና በኒቃብ አስከብሪ።
➡️ኢማሙ አሻፊኢ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ፦
''አንዴ በመንገድ የተጓዝኩኝ ያለ የአንዲትን ልጅ አገረድ ባት በድንገት ተመለከትኩኝ ከዚያም የተማርኩትን መሀፈዝ ከበደኝ አቃተኝ ይህንንም ጉዳይ ወኪዓ ለሚባሉ ሸይኼ አማከርኳቸው እነሱም ወንጀልን ቀንስ ተው በማለት አመላከቱኝ ይላሉ''።
🗝እንኛስ ስንቱን አላህ ያልፈቀደውን ነገር እንመለከታለን? ከሙሰልሰል ድራማ ጀምሮ አላህ በራህመቱ አይን ይመልከተን እንጂ።
አላህን ልንፈራ ይገባል።➡️
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَلْتَنظُرْ نَفْسٌ مَّا قَدَّمَتْ لِغَدٍ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ ማንኛይቱም ነፍስ ለነገ ያስቀደመችውን ትመልከት፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡ ሱረቱል ሐሽር 18
..🖋AbuFewzanAselefy