ያስፈልጋል።
5. አምስተኛ ደረጃ ተውሒዱ በነብዩ صلى الله عليه وسلم መመሪያ መሠረት መሰራቱ ነው። ማለትም ተውሒዳችን ለአላህ ጥርት ያለና በአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم ሱንና መሠረት ትክክል እንዲሆን ተውሒዳችንን ከቢድዓና ከፈጠራዎች የጠራ ሆኖ ነብያችን ሠርተው ባሳዩን መንገድ የተሠራ መሆን አለበት። ሥራው ሱና ላይ የተሠራ መሆኑ ግድ ነው። ነብዩ صلى الله عليه وسلم ለባልደረቦቻቸው
إنَّه من يعش منكم فسيرى اختلافا كثيرا, فعليكم بسنَّتي وسنَّة الخلفاء الراشدين المهديِّين, تمسَّكوا بها وعضُّوا عليها بالنواجذ
ከናንተ ወስጥ የሚቆይ ሰው ብዙ ልዩነቶችን (ኢኽቲላፍ) ያያል። አደራችሁን ሱንናዬንና ቅኖችና የተመሩ የሆኑ ኸሊፋዎችን ሱንና በመከተል እሷን ጨብጡ በቅንጣጢዎቻችሁ አጥብቃችሁ ያዙ። ስለዚህ ሱንና የማይቀር ጉዳይ ነው።
6. ስድስተኛው ደረጃ የሚያበላሸውን ነገር ከመስራት መጠንቀቅ ነው። ተውሒድን ከሚያበላሹ ነገሮች (ነዋቂዱ አተውሒድ) መጠንቀቅ ያስፈልጋል። ሽርክና ኩፍር ውስጥ ላለመውደቅ መጠንቀቅ ያስፈልጋል። ነብዩ صلى الله عليه وسلم ሁል ቀን ኩፍር ውስጥ ከመውደቅ አላህ እንዲጠብቃቸው ይለምኑት ነበር። አላህ ሆይ ከኩፍር ባንተ እጠበቃለሁ (አላሁመ ኢኒ አዑዙ ቢከ ሚነል ኩፍር) ይሉ ነበር። ኢብራሂም ዐ.ሰ. ጌታቸውን እየፈሩ وَٱجۡنُبۡنِي وَبَنِيَّ أَن نَّعۡبُدَ ٱلۡأَصۡنَامَ “እኔንም ልጆቼንም ጣዖታትን ከመገዛት አርቀን” እያሉ ይለምኑ ነበር። ይህ የሳሊሆች መንገድ ነው። ራሳቸው ላይ ጥመትን ይፈራሉ። የነብዩ صلى الله عليه وسلم በራሳቸው ላይ ንፍቅናን ይፈሩ ነበር። እንደዚሁም ታቢዒኖችም ይፈሩ ነበር። ሳሊሆችም እንዲሁ ናቸው። ሱፍያኑ ሰውሪይ ረሒመሁላህ أخاف أن أكون في أمِّ الكتاب شقيّا أخاف أن أُسلب الإيمان عند الموت ”በዋናው መፅሐፍ ውስጥ ሸቂይ (ጠመማ) ተብዬ እንዳልሆን እፈራለሁ፤ በመሞቻዬ ጊዜ ኢማንን እንዳልነጠቅ እፈራለሁ“ ይል ነበር። አንተ ሳታውቅ ስራህ እንዳይበላሽ መፍራትና መጠንቀቅ ግድ ነው።
أَن تَحۡبَطَ أَعۡمَٰلُكُمۡ وَأَنتُمۡ لَا تَشۡعُرُونَ
እናንተ የማታውቁ ስትኾኑ ሥራዎቻችሁ እንዳይበላሹ (ተከልከሉ)።
እውነታው ተውሒድን የሚያፈርሱ ነገሮችን በማወቅና በመራቅ ካልሆነ በስተቀር መጠንቀቅ ሊመጣ አይችልም። ስለዚህ እውቀት የግድ አስፈላጊ ነው።
7. ሰባተኛውና የመጨረሻው ደረጃ ፅናት ነው። በአላህ ትዕዛዝ ላይ አላህ ጋ እስክትገናኝ ድረስ ፀንቶ መቆየት ነው። ጌታን እስከምትገናኝ ድረስ በተውሒድ ላይ መፅናት ነው። አላሁ ተዓላ አለ
وَٱعۡبُدۡ رَبَّكَ حَتَّىٰ يَأۡتِيَكَ ٱلۡيَقِينُ
እውነቱም (ሞት) እስኪመጣህ ድረስ ጌታህን ተገዛ።
ኢማሙ ሙሐመድ ኢብን ዓብዱል ወሃብ ረሒመሁላህ
قال محمد ابن عبد الوهاب رحمه الله: المرتبة السابعة الثباتُ على الحقِّ والخوفُ من سوءِ الخاتمة لقوله صلى الله عليه وسلم إنَّ منكم من يعملُ بعمل أهل الجنَّةِ ويُختم له بعمل أهل النار
“ሰባተኛው ደረጃ በሐቅ ላይ መፅናትና ከመጥፎ መጨረሻ (ሱኡል ኻቲማህ) መፍራት ነው። ነብዩ صلى الله عليه وسلم ‘ከናንተ ውስጥ የጀነት ሰዎችን ስራ የሚሰራና በእሳት ሰዎች ስራ መጨረሻው የሚደረግለት አለ።’ ብለዋልና።” ብሏል።
ይህም በተጨማሪ ሳሊሆች ከሚፈሯቸው ትላልቅ ነገሮች ውስጥ አንዱ ነው። ይህ መፍራት በዘመናችን በጣም ትንሽ ነው። በዚህና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ በምታቃቸው ሰዎች ሁኔታ ማስተንተን በርካታ የማታቃቸውን ነገሮችን ያመላክትሀል። አላሁ አዕለም። የአላህ ባሮች ሆይ ፅናት! አላህ ጋር እስከምንገናኝ ድረስ በተውሒድ ላይ ፅናት! በዚህም ምክንያት የነብዩ ዱዓእ አብዛኛው يامقلب القلوب ثبت قلبي على دينك “አንተ ልቦችን ገለባባጭ የሆንክ ጌታዬ ሆይ ልቤን በሀይማኖትህ ላይ አፅና!” የሚል ነበር። አንተ ባሪያ ሆይ! በአላህ ችሮታ እንጂ ወደ ተውሒድ አልተመራህም! በአላህ እዝነት ነው። አንተ ብትጠም ይህ በአላህ ፍትህ ነው። የፈለገውን ሰው በችሮታው ይመራዋል፤ ይጠብቀዋል፤ ሰላም ያደርገዋል። የፈለገውን ደግሞ ፍትሀዊ ሲሆን ያጠመዋል፤ ረዳት የለሽ ያደርገዋል፤ ይፈትነዋል። ሁሉም በአላህ ፍላጎት (መሺአው) ውስጥ በቸርነቱ እና በፍትሀዊነቱ መካከል ይገለባበጣሉ። በመሆኑም አላህ በእዝነቱና በችሮታው መራን። ስለዚህ የአላህ ባሮች ሆይ ፅናት የሚሆነው በአላህ ችሮታ ነው። ግለሰቡ በራሱ ላይ በመደነቅ ወይም በፅናቱ አይደለም። እናም ፅናትን እንዳትነፈግ ጥናቃቄ ያስፈልጋል። ስለዚህ ወደ አላህ መጠጋትና እንዲያፀናህ ለሱም በመተናነስ መጠየቅ አለብህ። يامقلب القلوب ثبت قلبي على دينك
ኢንሻአላህ ይቀጥላል።
☟ SHARE ☟
http://T.me/History_Written_in_Blood