11. ሌላው ከተውሒድ ትላልቅ ትሩፋቶችና በረከቶች ውስጥ አንዱ ከአስቀያሚ ወንጀሎች (ፈዋሒሽ) መጠበቅ ነው። አዎ! ተውሒድ ባለቤቱን ቁጥብ እንዲሆንና ከአስቀያሚ ነገሮች እንዲጠበቅ ከሚያደርጉት ነገሮች ውስጥ ዋናው ነው። ይህም አንድ የአላህ ባሪያ ተውሒዱንና አላህን መፍራቱ ሲያረጋግጥ በእሱና በወንጀል መካከል ግርዶሽ ይሆንለታል። አላህ ሱ.ወ. ዩሱፍን በኢኽላሱና በተውሒዱ ምክንያት ከኅጢአትና መጥፎ ነገር ጠብቆታል። አዎ! ራሳችንን ከኅጢአት ለመጠበቅ የተውሒድ ሚና እንዴት ትልቅ ነው! ሙስሊሙን ማህበረሰብ ከዝቅጠትና ኅጢአት ለመጠበቅ የተውሒድ ሚና ምን ያህል ትልቅ ነው! አላህ ሱ.ወ. ስለዩሱፍ እንዲህ ብሏል።
كَذَٰلِكَ لِنَصۡرِفَ عَنۡهُ ٱلسُّوٓءَ وَٱلۡفَحۡشَآءَۚ إِنَّهُۥ مِنۡ عِبَادِنَا ٱلۡمُخۡلِصِينَ
እንደዚሁ መጥፎ ነገርንና ኀጢአትን ከእርሱ ላይ ልንመልስለት (አስረጃችንን አሳየነው)። እርሱ (ተውሒድን) ለአላህ ብቻ ካጠሩ ባሮቻችን ነውና ።
በሐፍስ አቀራር ደግሞ
كَذَٰلِكَ لِنَصۡرِفَ عَنۡهُ ٱلسُّوٓءَ وَٱلۡفَحۡشَآءَۚ إِنَّهُۥ مِنۡ عِبَادِنَا ٱلۡمُخۡلَصِينَ
እንደዚሁ መጥፎ ነገርንና ኀጢአትን ከእርሱ ላይ ልንመልስለት (አስረጃችንን አሳየነው)። እርሱ ከተመረጡት ባሮቻችን ነውና።
ማለትም በዩሱፍ ኢኽላስ (ስራውን ለአላህ ብቻ ማጥራት) ምክንያት አላህ ከሱ ወንጀልንና መጠፎ ነገርን አስወገደለት፤ በጥብቅነትም አጣቀመው። “እርሱ (ስራቸውን) ለአላህ ብቻ ካጠሩ ባሮቻችን ነውና።” ጌታውን አንድ አድርጎ ተገዛ፤ ሀይማኖቱንም አጠራ። ምንዳውም “እርሱ ከተመረጡት ባሮቻችን ነውና።” የሚል ሆነ። አላህ ከወንጀልና መጥፎ ነገሮች አጠራው። ‘ኢነሁ ሚን ዒባዲነል ሙኽሊሲን’ ላምን በከስራ ሲነበብ ዩሱፍ ጌታውን አንድ አድርጎ ተገዛ፤ ሀይማኖቱንም አጠራ። ምንዳው ደግሞ ‘ሙኽለሲን’ ሆነ። ላምን ፈትሀ ተደርጎ ሲነበብ ማለትም አላህ ከወንጀልና መጥፎ ነገሮች አጠራው። በዚህም ምክንያት ከፊሎቹ እንዳሉት ኢማን ልቡ ውስጥ የገባና በሁሉም ጉዳዮቹ ውስጥ ለአላህ ያጠራ የሆነ ሰው ለኢማኑና ለኢኽላሱ ምንዳ የሚሆን አላህ በኢማኑ ብርሃንና በኢኽላሱ እውነተኝነት ከመጥፎ ነገርና ከወንጀል ዓይነቶችና ለወንጀል ሰበብ ከሚሆኑ ነገሮች ከሱ ይከላከልለታል። ለዚህም አላህ ሱ.ወ. አለ “እንደዚሁ መጥፎ ነገርንና ኀጢአትን ከእርሱ ላይ ልንመልስለት (አስረጃችንን አሳየነው)። እርሱ (ተውሒድን) ለአላህ ብቻ ካጠሩ ባሮቻችን ነውና ።” ስራውን ለአላህ ባጠራ ጊዜ አላህም አጠራው፤ ከመጥፎ ነገርና ከወንጀል ጠበቀው። ተውሒድ ለአንድ የአላህ ባሪያና ለጀመዓ የሚያመጣው በረከት እንዴት ትልቅ ነው! በዱንያና በአኼራ ያሉት በረከቶቹ እንዴት ትልቅ ናቸው። አላህ ሆይ ከኛ ተቀበለን አንተ ሰሚና ተመልካች ነህ!
ይቀጥላል ኢንሻአላህ
☟ SHARE ☟
http://T.me/History_Written_in_Blood