በዓብዲ ኢብንሑመይድ ሙስነድ ውስጥ እንደተዘገበው መርፉዕ በሆነ ሐዲስ ከጭንቅ ነፃ መውጫ ቃል ‘ላኢላሀ ኢለላህ አልዐዚሙ አልሐሊም’ (ከትልቁ ቻዩ አላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም) ነው። ይህች ትልቅ ንግግር ነፃ መውጫ ቃል ተባለች። እንደዚሁም አሕመድ፣ አቡዳውድ፣ ነሳኢና ኢብኑ ማጃህ እንደዘገቡትና አስማእ ቢንት ዑመይስ ረ.0. እንዳተናገረችው
حديث أسماء بنت عُميس - رضي الله عنها – قالت: قال لي رسول الله صلى الله عليه وسلم ألا أعلِّمُكِ كلماتٍ تقولينَهُنَّ عند الكربِ, اللهُ اللهُ ربِّي لا أشركُ به شيئا
የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم ”በሀዘን ጊዜ የምትያቸው ንግግሮችን ላስተምርሽ ወይ? ‘አላህ አላህ ጌታዬ ነው በሱ ምንም አላጋራም’“ አሉኝ ብላለች።
أخرج النسائي والحاكم من حديث سعد ابن وقَّاص - رضي الله عنه - قال: كنَّا جلوسا عند رسول الله صلى الله عليه وسلم قال ألا أخبركم أو أحدِّثُكم بشيءٍ إذا نزل برجلِ منكم كربٌ أو بلاءٌ من بلاء الدنيا دعا به ففُرِّج؟ فقيل له بلى, قال دعاءُ ذي النون لَّآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنتَ سُبۡحَٰنَكَ إِنِّي كُنتُ مِنَ ٱلظَّـٰلِمِينَ
ነሳኢና አልሐኪም በዘገቡት ሐዲስም ሰዕድ ኢብን አቢ ወቃስ ረ.ዐ. ረሱል صلى الله عليه وسلم ዘንድ ተቀምጠን ነበር። “ከናንተ ውስጥ አንድ ሰው ሀዘን ወይም ከዱንያ ፈተናዎች የሆነ አንድ በላእ (ፈተና) በደረሰበት ጊዜ በሱ አላህን የሚለምንበትና ከሱ ነፃ የሚወጣበትን ዱዓእ ልንገራችሁ ወይ?” አሉ፤ አዎ ንገሩን አልናቸው። “የዚንኑን[1] ዱዓእ ነው ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ የለም። ጥራት ይገባህ። እኔ በእርግጥ ከበዳዮቹ ነበርኩ” አሉን።
አስተውል አንተ የአላህ ባሪያ ሆይ! ነብዩ صلى الله عليه وسلم ችግር በበረታባቸውና ሀዘን በደረሰባቸው ጊዜ እንዴት ነበር የሚያደርጉት። በተውሒድ ይጠበቃሉ፤ በሱም አላህን ይለምናሉ፤ ወደ አላህም ይቃረቡ (ተወሱል ያደርጉ) ነበር። ይህንን ነገር ያስተዋለ ሰው የተውሒድን ውጤትና ሀዘንና ችግሮች ለማራቅና ሀሳብን ለማስወገድ በእሱ መቃረብን ያውቃል። የሩሱሎች ፈለግ በችግር ጊዜ ወደ አላህ በተውሒድ ይቃረቡ ነበር። ይሄው ነብዩላህ ዩኑስ ትልቅ ችግር የደረሰበት ጊዜ ተውሒዱን መቃረቢያ (ተወሱል) አድርጎ ወደ ፈጣሪውና ወዳጁ ተጠጋ ተጠበቀ። አላህ አለ
وَذَا ٱلنُّونِ إِذ ذَّهَبَ مُغَٰضِبٗا فَظَنَّ أَن لَّن نَّقۡدِرَ عَلَيۡهِ فَنَادَىٰ فِي ٱلظُّلُمَٰتِ أَن لَّآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنتَ سُبۡحَٰنَكَ إِنِّي كُنتُ مِنَ ٱلظَّـٰلِمِينَ ٨٧ فَٱسۡتَجَبۡنَا لَهُۥ وَنَجَّيۡنَٰهُ مِنَ ٱلۡغَمِّۚ وَكَذَٰلِكَ نُـۨجِي ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
የዓሳውንም ባለቤት ተቆጥቶ በኼደ ጊዜ (አስታውስ)። በእርሱም ላይ ፈጽሞ የማንፈርድበት መኾናችንን ጠረጠረ። (ዓሳም ዋጠው)። በጨለማዎችም ውስጥ ኾኖ ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ የለም። ጥራት ይገባህ። እኔ በእርግጥ ከበዳዮቹ ነበርኩ በማለት ተጣራ። ለርሱም ጥሪውን ተቀበልነው። ከጭንቅም አዳነው። እንደዚሁም ምእመናንን እናድናለን።
መልሱ የመጣበትን ፍጥነት ተመልከት “ለርሱም ጥሪውን ተቀበልነው።” ይህ ለዩኑስ ዐ.ሰ. ብቻ አይደለም። “እንደዚሁም ምእመናንን እናድናለን።” ይህ ደግሞ ኢብራሂም ዐ.ሰ. ነው፤ እሳት ውስጥ የተጣለ ጊዜ በተውሒድ ወደ አላህ እንጂ አልዞረም። حَسْبُنَا اللَّهُ وَنِعْمَ الْوَكِيلُ በቂያችንም አላህ ነው ምን ያምርም መጠጊያ! አለ። እሳቷም ቀዝቃዛና ሰላም ሆነችለት።
قُلۡنَا يَٰنَارُ كُونِي بَرۡدٗا وَسَلَٰمًا عَلَىٰٓ إِبۡرَٰهِيمَ ٦٩ وَأَرَادُواْ بِهِۦ كَيۡدٗا فَجَعَلۡنَٰهُمُ ٱلۡأَخۡسَرِينَ ٧٠ وَنَجَّيۡنَٰهُ وَلُوطًا إِلَى ٱلۡأَرۡضِ ٱلَّتِي بَٰرَكۡنَا فِيهَا لِلۡعَٰلَمِينَ
«እሳት ሆይ! በኢብራሂም ላይ ቀዝቃዛ፤ ሰላምም ሁኚ» አልን። በእርሱም ተንኮልን አሰቡ። በጣም ከሳሪዎችም አደረግናቸው። እርሱንና ሉጥንም ወደዚያች በውስጧ ለዓለማት በረከትን ወደ አደረግንባት ምድር (በመውሰድ) አዳንናቸው።
ከሁለቱም በፊት ደግሞ ነቢዩላህ ሁድ ዐ.ሰ. ህዝቦቹ በኃይልና በጉልበት ትልቅና የእነሱ አምሳያ በሀገሮች ውስጥ ያልተፈጠረ ከመሆናቸው ጋር ድርቀታቸውንና ኩፍር ላይ ሙጥኝ ማለታቸውን ባየ ጊዜ በተውሒድ ዛተባቸው።
قَالُواْ يَٰهُودُ مَا جِئۡتَنَا بِبَيِّنَةٖ وَمَا نَحۡنُ بِتَارِكِيٓ ءَالِهَتِنَا عَن قَوۡلِكَ وَمَا نَحۡنُ لَكَ بِمُؤۡمِنِينَ ٥٣ إِن نَّقُولُ إِلَّا ٱعۡتَرَىٰكَ بَعۡضُ ءَالِهَتِنَا بِسُوٓءٖۗ قَالَ إِنِّيٓ أُشۡهِدُ ٱللَّهَ وَٱشۡهَدُوٓاْ أَنِّي بَرِيٓءٞ مِّمَّا تُشۡرِكُونَ ٥٤ مِن دُونِهِۦۖ فَكِيدُونِي جَمِيعٗا ثُمَّ لَا تُنظِرُونِ ٥٥ إِنِّي تَوَكَّلۡتُ عَلَى ٱللَّهِ رَبِّي وَرَبِّكُمۚ مَّا مِن دَآبَّةٍ إِلَّا هُوَ ءَاخِذُۢ بِنَاصِيَتِهَآۚ إِنَّ رَبِّي عَلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ ٥٦ فَإِن تَوَلَّوۡاْ فَقَدۡ أَبۡلَغۡتُكُم مَّآ أُرۡسِلۡتُ بِهِۦٓ إِلَيۡكُمۡۚ وَيَسۡتَخۡلِفُ رَبِّي قَوۡمًا غَيۡرَكُمۡ وَلَا تَضُرُّونَهُۥ شَيۡـًٔاۚ إِنَّ رَبِّي عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٍ حَفِيظٞ ٥٧ وَلَمَّا جَآءَ أَمۡرُنَا نَجَّيۡنَا هُودٗا وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مَعَهُۥ بِرَحۡمَةٖ مِّنَّا وَنَجَّيۡنَٰهُم مِّنۡ عَذَابٍ غَلِيظٖ ٥٨
አሉ፡- «ሁድ ሆይ! በአስረጅ አልመጣህልንም። እኛም ላንተ ንግግር ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው አይደለንም። እኛም ለአንተ አማኞች አይደለንም። «ከፊሎቹ አማልክቶቻችን በክፉ ነገር (በዕብደት) ለክፈውሃል እንጂ ሌላን አንልም» (አሉ)። «እኔ አላህን አስመሰክራለሁ። ከምታጋሩትም እኔ ንጹሕ መሆኔን መስክሩ» አላቸው። ከእርሱ ሌላ (አማልክትን ከምታጋሩት ንጹህ ነኝ)። ሁላችሁም ሆናችሁ ተንኮልን ሥሩብኝ፤ ከዚያም አታቆዩኝ። «እኔ በጌታዬና በጌታችሁ በአላህ ላይ ተጠጋሁ። በምድር ላይ ምንም ተንቀሳቃሽ የለችም እርሱ አናትዋን የያዛት ብትሆን እንጂ። ጌታዬ (ቃሉም ሥራውም) በቀጥተኛው መንገድ ላይ ነው» (አላቸው)።«ብትዞሩም በእርሱ ወደእናንተ የተላክሁበትን ነገር በእርግጥ አድርሼላችኋለሁ። ጌታዬ ከእናንተ ሌላ ሕዝብም ይተካል ምንም አትጎዱትምም። ጌታዬ በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነውና» (አላቸው)። ትዕዛዛችንም በመጣ ጊዜ ሁድንና እነዚያን ከእሱ ጋር ያመኑትን ከእኛ በሆነው ችሮታ አዳን። ከብርቱ ቅጣትም አዳናቸው።