ክለባችን አርሰናል በተለያዩ አጥቂዎች ስሙ እየተነሳ ያለ ሲሆን በአሁኑ ሰዐት ክለባችን ከኢዛክ ፣ እና ከኦሊሴ ጋር ስሙ በጣም እንደተቀራረበ የሚታወስ ዜና ነው።
በሌላ መረጃ ስንመለከትም የሊዝበኑን አጥቂ ቪክቶር ጂዮክሬስንም ለማስፈረም እንደሚፈልግ ተነግሯል ፣ አርሰናል ከዚህ በፊትም በተጫዋቹ ላይ ፍላጎት ቢኖረውም ልክ እንደ ቼልሲ የመሰሉ ሌሎች ክለቦች ተጫዋቹን ለማስፈረም መቅረባቸውን ተከትሎ ዝውውሩን ገታ አድርጎት ነበር ኑገር ግን በአሁን ሰዐት ላይ ትልቅ ኢላማቸው ቪክቶር ጂዮኮሬሽ ነው።
ሌላኛው ደግሞ የንቦቹ ብሬንትፎርድ አጥቂ ኢቫ ቶኒ ነው ፣ እርሱ ከባለፈው የክረምት የዝውውር መስኮት አንስቶ የክለባችን ትልቅ ኢላማ እንደነበር የማይዘነጋ ሲሆን አሁንም የክለባችን ትልቁ ኢላማ ነው ነገር ግን ተጫዋቹ ላይመጣበት የሚችልበት ምክንያት ብሬንትፎርድ ለተጫዋቹ የገመቱት ሂሳብ ውድ በመሆኑ ላይመጣሹት የሚችልበትም እድል አለ።
ሌላኛውና የመጨረሻው የተባለው የአሮጊቶቹ አጥቂ እና ብዙዎች የሚስማሙበት ዱዛን ቭላሆቪች ነው እርሱም ስሙ ከክለባችን ጋር ከተያያዘ ሰንበትበት ብሏል ፣ ከጥር ዝውውር መስኮት ጀምሮ ስሙ ከክለባችን ጋር ሲነሳ ቆይቷል ፣ አሁንም በክለባችን ራዳር ላይ እንደሆነ ተነግሯል።
SHARE''
@ETHIO_ARSENAL